የፀሐይ ጋዝና የመገናኛ ሳቴላይቶች | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 08.06.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የፀሐይ ጋዝና የመገናኛ ሳቴላይቶች

በምድራችን የአየር ንብረት ላይና በሌላውም ተጽእኖ ሊኖራቸው ስለሚችል በኅዋ ስለሚከሠቱ አንዳንድ ነገሮች ፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ሳይንስና ሥነ-ቴክኒክ መበጀቱ የሚያራጥር አይደለም።

default

ለምድራችን በቂ ብርሃንና ሙቀት የምታድለው የተፈጥሮ እቶን እሳት፣ ፀሐይ፤ የአሜሪካው ብሔራዊ የበረራና የኅዋ አስተዳደር፤ በመባል የሚታወቀው መሥሪያ ቤት፣ በእንግሊዝኛው ምህጻር (NASA)፣ ሰሞኑን ከዚያው ከፀሐይ ፣ የኑክልየር ፍም ከሆነው አካልዋ እሳተ ገሞራ መሰል እሳት ይበልጥ በመተፋቱ፣ ከዚያ የሚነሳው ፀሐያዊ ነፋስ ፤ ዛሬም ሆነ በሚመጡት ቀናት የተወሰነም ቢሆን የሳቴላይት ግንኙነቶችን እንደሚያውክ ገልጿል። ብሔራዊው የአየር ጠበይ ምርምር አገልግሎትም እንዳለው እ ጎ አ ከ 2006 ዓ ም ወዲህ፤ በፀሐይ አካል ላይ የኑክልየር ፍም ፍንዳታ በማየሉ፣ የመልክዓ-ምድራዊው መግነጢሳዊ ጨረር ፤ በመጠኑም ቢሆን መታወኩ አይቀርም። አምና የተቋቋመው የ NASA የፀሐይ ባህርይ ተከታታይ ማዕከል፤ ሰለፀሐይ የአሳት ማዕበል ያናሣው ፎቶግራፍና ተንቀሳቃሽ ምስል፤ ሲያዩት «የሚያስደንቅ» መሆኑን ነው የገለጸው። በሌላ በኩል የእቶኑ ፍንዳታ በቀጥታ ወደ ምድር ያነጣጠረ ባለመሆኑ የሚያስድረው ተጽእኖ ከሞላ ጎደል ቀለል ያለ ነው።

ከፀሐይ አካል የኑክልየር ፍም የሚደርሰው ፍንዳታ፤ የሚተፋውና በኅዋ የሚያሠራጨው ጋዝ ሲሆን፤ መግነጢሳዊ ኅይልም አለበት። በመሆኑም ጠበብት፤ በፀሐይና በምድራችን መካከል የ 150 ሚሊዮን ኪሎሜትር ርቀት ቢኖርም፤ በመግነጢሳዊ የጨረር መነሻና መድረሻ ግጭት ይፈጠራል አይፈጠርም ጉዳዩን በጥብቅ ይከታተላሉ።

ከ 12 እስከ 24 ሰዓት የሚያጋጥመው የመልክዓ ምድር መግነጢሳዊ ማዕበል፣ ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ አንድ ሰዓት ገደማ አንስቶ እንደሚከሠት ነው የተነገረው። ይህም በኃይለኛነቱ እ ጎ አ በ 2006 ዓ ም በታኅሳስ ወር ካጋጠመው ጋር ተመሳሳይ ሳይሆን እንደማይቀር ነው የተነገረው።

12 የሚሆኑ ሳቴላይቶችና የጠፈር መንኮራኩር ፣ በኅዋ የ«ሄሊዮስፌር» እርከን ላይ ከፀሐይ የሚነጠቀውን የጨረር መጠንና የሚያስከትለውን ተጽእኖ ይከታተላሉ። በጨረቃ ዙሪያ የሚሽከረከር አንድ ሌላ መንኮራኩርም፤ ተመሳሳይ ክትትል ያደርጋል።

በፀሐይ አካል የሚነሳው ፍንዳታ ፤ በኤልክትሪክ ኃይል ማሠራጫ አውታሮች ምድር ላይ የመርከቦችን፣ አየር ላይ ፣ የአኤሮፕላኖችንና የሌሎችንም የጉዞና የበረራ አቅጣጫ መጠቆም እንዳይቻል ሊያሠላክል ይችላል። በዚህ ሳቢያ፤ በሰሜን የምድር ዋልታ በኩል የሚበሩ የህዝብ ማመላላሻ አኤሮፕላኖች ፣ የበረራ አቅጣጫ እንዲለውጡ ይገደዱ ይሆናል። ይህን ለማድረግ የሚገደዱትም በበረራ ወቅት የመገናኛ መሣሪያዎቻቸው መሠናክል እንዳያጋጥማቸው በመሥጋት ነው። ዛሬም ሆነ ነገ፤ በሰሜንና ደቡብ ዋልታ ሲመሻሽ፣ («አውሮራ ቦራሊስና አውሮራ አውስታራሊስ)የሰሜናዊና ደቡባዊ ደማቅ የብርሃን ፍንጠቃም ሳይታይ እንደማይቀር ተመልክቷል።

(ሙዚቃ)---------------

«ድምፅ ሳያሰማ ከሰማይ የሚወርድ የእሳት ኳስ አየሁ» ሲል፤ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 15ኛው ምዕተ ዓመት፣ የጥንታዊቷ ግብፅ ንጉስ (ፈርዖን) ፣ ቱትሞሲስ ሣልሣዊ ተናግሮ ነበር። ምንነቱ በውል ስላልታወቀ እንቅብ መሰል ብርሃን ፈንጣቂ በራሪ ነገር ከጥንት ጀምሮ ይነገር እንደነበረ የፈርዖኑ ቃል አንድ ምሥክር ነው ።

የሚገርመው ይህ ዓይነቱ ተረት መሰል ትረካ፤ በዛሬው ዘመን ሰዎችም ዐቢይ ትኩረት ተሰጥቶት ክትትል የሚደረግ መሆኑ ነው። የጥንታ ግብጻውያን ያን መሰል ትረካ ሲመዘግቡ፤ በአሁኑ ዘመን ከሚገኙትም አንዳንድ አስደናቂ ነገሮች መሰማታቸው አልቀረም። ባለፈው ታኅሳስ ወር ፤ የካይሮ ዩኒቨርስቲ የጥንት ቅርሳ ቅርስ ጥናት ተመራማሪና የዚሁ ክፍል መሪ ዶ/ር አላ ሻሒን ፤ ለተሰበሰበ ህዝብ ባሰሙት ንግግር ላይ፣ በ ጊዜ የሚገኙትን ፒራሚዶች በመገንባት ረገድ ሌሎች ፍጡራን ፤ የጥንት ግብጻውያን ሳይረዱ አልቀሩም የሚለው መላ ምት፤ ምናልባት እውነትነት ሳይኖረው አይቀርም ሲሉ መናገራቸው ተጠቅሷል። ፒራሚዶቹ፤ የሌሎች ፍጡራን (ከሰው ውጭ ማለት ነው) የሥነ ቴክኒክ አሻራ ይኖርባቸው ይሆን የሚል ጥያቄም ቀርቦላቸው፣ ማረጋገጥም ማስተባበልም አልችልም። ፒራሚዱ ሥረ መሠረትም ውስጥ፤« የሆነ የዚህ ዓለም ክፍል ያልሆነ ነገር ይገኛል፣ ማለታቸውም ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ነው።

በ 329 ዓመተ ዓለም፤ ብርማ ቀለም ያላቸው 2 አንጸባራቂ ጋሻዎች፤በታላቁ እስክንድር ጦር ሠራዊት ላይ በተደጋጋሚ መውደቃቸው፤ በታሪክ ተመዝግቧል። እ ጎ አ ሚያዝያ 15 ቀን 1561 ዓ ም፤ ጀርመን ውስጥ ኑዑረንበርግ ላይ ፣ ጥቁር ፤ ቀይ ና ብርቱካናማ ቀለም እንዲሁም ሰማያዊና ነጭ ከረጢት መሰል አሎሎ ከሰማይ መውረዱ የተመዘገበ ጉዳይ ነው። ሜክሲካዊው የሥነ-ፈለክ ምሁር ፣ ሆሴ ቦኒያ፣ እ ጎ አ በነሐሴ 12 እና 13 ,1883 ፤ የተለያየ ቅርጽ ያላቸው 400 የሰማይ አካላት በፀሐይ በኩል ሲያልፉ ማየቱን ጽፏል። አሌክሳንደር ሐሚልተን የተባለ አሜሪካዊ አርሶ አደር እ ጎ አ ሚያዝያ 28 ቀን 1897 ዓ ም፤ አንድ ባየር የሚንሳፈፍ መርከብ መሰል ነገር ከጋጥ አንዲት ላም ጭኖ መወሰዱን፤ በማግሥቱም የላሚቱ አንገት ቆዳና እግርቿ ፣ በጎረቤት ጓሮ ውስጥ ተበታትኖ መገኘቱን ዘግበዋል።

ምንነቱ ስለማይታወቅ በራሪ አካል በቅርብ ጊዜው ከተነገሩት ታሪኮች አንዱ ኬኔት አርኖልድ የተባሉት አሜሪካዊ ፖሊስ፤ በዋሽንግተን ፌደራል ክፍለ ሀገር ያጋጠማቸው ልዩ ሁኔታ ነው። በራሳቸው አኤሮፕላን በረራ ላይ እንዳሉ፣ አንድ ጠፍጣፋ ሣህን መሰል በራሪ መሣሪያ በግምት በሰዓት 1,600 ኪሎሜትር በመክነፍ በአጠገባቸው በርሮ መሠወሩን በጊዜው ያሳወቁ ሲሆን «የሚታመኑ ዜጋ» ናቸው በመባሉም የሰጡት ቃል በጊዜው ተደማጭነት አግኝቶ ነበር።

ከዚያ ወዲህ ፤ በብዙ መቶ ሺ የሚቆጠር ተመሳሳይና ለየት ያለም ታሪክ፤ ምንነታቸው እስካሁን ጥርት ብሎ ሊታወቅ ስላልተቻለው በራሪ ነገሮችና አብራሪዎቻቸው ተዘግቧል።

ይህ ዓይነቱ ትረካ በአንድ አካባቢ ብቻ ሳይሆን በዓለም ዙሪያ ፤ ምትኀት ይሁን እውነት በሰፊው ይነገራል። ይህን በተሻለ ሁኔታ መከታተል የሚችሉት በኢንዱስትሪ ይበልጥ የገሠገሡት፤ በተለይም መንኮራኩር የሚያመጥቁት አገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። እውን፤ ከሌላ ዓለማት እየመጡ ምድራችን የሚጎበኙ ልዩ ፍጡራን አሉ? እስካሁን ይህ ጉዳይ በተጨባጭ መረጃ ለህዝብ የቀረበበት ሁኔታ የለም። መንግሥታት በአየር ግዛታቸው የሚከሠቱ ለየት ያሉ ሁኔታዎችን በተመለከተ፤ በመከላከያ መሥሪያ ቤታቸው፤ በምሥጢር ከመያዝ በስተቀር በህዝብ ዘንድ እንዲታወቅ አያደርጉም ነበር። ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ ግን ፤ ፈረንሳይ ብሪታንያና ሌሎችም አንዳንድ ያነሷቸውን ፎቶግራፎችና ታሪኮችንም ለህዝብ ማቅረብ ጀምረዋል። የብሪታንያ መንግሥት፤ ባለፈው መጋቢት፣ በመከላከያው መ/ቤትና በህዝቡም እ ጎ አ ከ 1950ኛዎቹ ዓመታት አንስቶ ከተሰበሰቡት ምንነታቸው በውል ተለይቶ ያልታወቀ በራሪ ነገሮችን ከሚመለከቱ ፋይሎች መካከል ፤ 35ቱን በታዩበት ቦታ በዘጋቢ ፊልም ረዳትነት አቅርቧል። ልዩ ፍጡራን አፍነው ወስደውኝ ነበረ እያሉ የሚናገሩም አሉ። አንዱ በተጠቀሰው ወር መጽሐፍ ጽፎ ፤ በልዩ ፍጡራን ታፍኜ ነበረ ሲል ያስታወቀው ፤ ፋን ሃለን የተሰኘው የሙዚቃ ቡድን የቀድሞ ጊታር ተጫዋችና መሪ አቀንቃኝ ነው።

የአውስትሬሊያ የመከላከያ ሠራዊት የሰበሰበውን ፤ አስገራሚ ስለሚባሉት እንቅብ መሰል በራሪ ነገሮች የሰበሰባቸው ፋይሎች የጠፉበት መሆኑን በትናንቱ ዕለት አስታውቋል። ሲድኒ ሞርኒንግ ሔራልድ የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ ፤ ህዝብ በዚህ ረገድ ለማወቅ የሚፈልጋቸውን አንዳንድ ሰነዶች የመከላከያው መሥሪያ ቤት ይፋ እንዲያደርግ ተጠይቆ 2 ወራት ፈልጎ ሊያገኛቸው አልቻለም። የአውስትሬሊያ የመከላከያ ኃይል፤ ምንነታቸው የማይታወቅ በራሪ ነገሮች ስለሚያልፉባቸው አካባቢዎችም ሆነ ስለታዩባቸው ቦታዎች መዘገብ ካቆመ 11 ዓመት ሆኖታል። በአንጻሩ፤ ህዝቡ የሆነ ልዩ በራሪ ነገር ካየ ለፖሊስ ብቻ እንዲያመለክት መክሯል። በምድር ከምንኖረው ሰዎች ውጭ ፤ ሌሎች ፍጡራን ምናልባት በሌሎች ፕላኔቶች ይኖሩ እንደሁ ኮሽ የሚል ድምፅም ቢሆን የሚያዳምጥ ፤ ዩናይትድ እስቴትስ ውስጥ በሰሜን ካሊፎርኒያ ተተክሎ የነበረው ልዩው ቴሌስኮፕ፣ በበጀት ሳቢያ ባለፈው ወር ሥራውን ማቆሙ አይዘነጋም።

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ

ተዛማጅ ዘገባዎች