የጨለንቆው ግጭት  | ኢትዮጵያ | DW | 12.12.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጨለንቆው ግጭት 

እንደ አይን ምስክሩ ሰዎቹ የተገደሉት፣ ከጨለንቆ ወጣ ብላ በምትገኝ የሶማሌ ክልል አዋሳኝ መንደር ውስጥ አንድ ሰው በልዩ ፖሊስ ተገድሏል መባሉ ከተሰማ በኋላ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በተነሳ ግጭት ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:04

የጨለንቆው ግጭት

ምሥራቅ ሐርርጌ ጨለንቆ ውስጥ ትናንት በተቀሰቀሰ ግጭት የሞቱ ሰዎች የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ መፈፀሙን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ። ዛሬ የአስራ አንድ ሰዎች ቀብር በተፈፀመበት ቦታ ላይ መገኘታቸውን ለዶቼቬለ የተናገሩ አንድ የከተማዋ ነዋሪ እንዳሉት ከሟቾቹ መካከል ተማሪዎች ይገኙበታል። እንደ አይን ምስክሩ ሰዎቹ የተገደሉት፣ ከጨለንቆ ወጣ ብላ በምትገኝ የሶማሌ ክልል አዋሳኝ መንደር ውስጥ አንድ ሰው በልዩ ፖሊስ ተገድሏል መባሉ ከተሰማ በኋላ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በተነሳ ግጭት ነው። የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት  የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ  ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በግጭቱ ቢያንስ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን እና 14 መቁሰላቸውን በፌስ ቡክ ማሳወቃቸው ተዘግቧል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉትን የዓይን ምስክር ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት አነጋግሬያቸዋለሁ። 

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ 

Audios and videos on the topic