የጦር ሥልጠና ለፔሽመርጋ ተዋጊዎች በጀርመን | ዓለም | DW | 16.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የጦር ሥልጠና ለፔሽመርጋ ተዋጊዎች በጀርመን

የጀርመን ብሔራዊ ጦር በሰሜን ኢራቅ በ«አይ ኤስ» ወይም በእስላማዊው መንግሥት አንፃር ለሚዋጉት የኩርድ ፔሽመርጋ ተወላጆች የጦር ስልት ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፣ ጦሩ ለፔሽመርጋ ተዋጊዎች ሥልጠና ሲሰጥ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ አለመሆኑን የጀርመን መከላከያ ሚንስቴር አስታውቋል።

ለሥልጠና በጀርመን የሀምልቡርግ ከተማ የሚገኘው ሁለተኛው የፔሽመርጋ ተወላጆች ቡድን ከውጊያ ስልት ጎን የጦር መሳሪያ መፈታታት እና መግጠም፣ የተሰበሩ የጦር ተሽከርካሪዎችን መጠገን ፣ በተለይም፣ የተቀበሩ ፈንጂዎችን ፈልጎ ማምከንን እና በፀረ ታንክ ሮኬት በትክክል መጠቀም የሚያስችለው ትምህርት ይሰጠዋል።

ለቮልፍጋንግ ዲርክ/ይልማ ኃይለሚካኤል

አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic