1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የጦር መሳርያ የመቀማት ዓላማ የለንም » ፖሊስ

ሰኞ፣ ጥቅምት 29 2014

በአዲስ አበባ ከተማ የጦር መሳርያ የማስመዝገቡ  ሂደት የከተማዋን ደህንነት ለማስጠበቅ እንጂ የጦር መሳርያ የመቀማት ዓላማ እንደሌለው የከተማዋ ፖሊስ ገለጸ። በትግራይ ተወላጆች ላይ በጅምላ እስራት እየተፈጸመ ነው የሚለውን ክስ እንደማይቀበሉ  የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ  ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/42js6
Logo der Polizei-Kommission Addis Abebas
ምስል Addis Ababa Police Commission

«የጦር መሳርያ የመቀማት ዓላማ የለንም » የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ

«የጦር መሳርያ የመቀማት ዓላማ የለንም » ፖሊስ
በአዲስ አበባ ከተማ የጦር መሳርያ የማስመዝገቡ  ሂደት የከተማዋን ደህንነት ለማስጠበቅ እንጂ የጦር መሳርያ የመቀማት ዓላማ እንደሌለው የከተማዋ ፖሊስ ገለጸ። በትግራይ ተወላጆች ላይ በጅምላ እስራት እየተፈጸመ ነው የሚለውን ክስ እንደማይቀበሉ  የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ  ተናግረዋል። «ከፖሊስ ጋር ተባብረው የሚሰሩ እና ለፖሊስ መረጃ የሚሰጡ የትግራይ ተወላጆች አሉ» ያሉት ኮማንደር ፋሲካ የከተማዋን ደህንነት የማስጠበቁ ስራ በደሴ እና የኮምቦልቻ ከተሞች የተፈጠረውን አይነት ተመሳሳይ ችግር አዲስ አበባ ውስጥ እንዲከሰት ስለማንፈልግ ቁጥጥራችንን ጠበቅ አድርገናል ብለዋል ።
ነጋሽ መሐመድ አነጋግሯቸዋል።