የጦማሪ እና አራማጅ ዘላለም ወርቅአገኘሁ መፈታት | ኢትዮጵያ | DW | 30.01.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጦማሪ እና አራማጅ ዘላለም ወርቅአገኘሁ መፈታት

ደብርሃን ለተሰኘው ድረ-ገጽ በዋነኛነት ጽሁፎችን ያቀርብ የነበረው እና አራት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ በእስር ላይ የቆየው ጦማሪ እና አራማጅ (አክቲቪስት) ዘላለም ወርቅአገኘሁ ዛሬ ከእስር ተፈትቷል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:20

ጦማሪ እና አራማጅ ዘላለም ወርቅአገኘሁ ተፈታ

በግንቦት 2008 ዓ.ም ሽብርተኝነት በመርዳት ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ የተፈረደበት ዘላለም ወርቅአገኘሁ የእስር ጊዜውን ጨርሶ የተለቀቀው በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር ካለው ከዝዋይ ማረሚያ ቤት ነው፡፡ ዘላለም በ2001 ዓ.ም. በወጣው የጸረ-ሽብር ህግን ተላልፋሃል በሚል የተፈረደበት አምስት ዓመት ከአራት ወር ነበር። በቂሊንጦ፣ ቃሊቲ እና ዝዋይ ማረሚያ ቤቶች ለ3 ዓመት ከ7 ወር በእስር የቆየው ዘላለም ዛሬ ተፈትቶ ከቤተሰቡ ጋር ተገናኝቷል። ከእስር ከወጣ ከጥቂት ሰዓት በኋላ በስልክ ለዶይቼ ቬለ የሰጠውን አጠር ያለ ቃለ ምልልስ የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ ፡፡ 

ተስፋለም ወልደየስ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic