የጥፋተኝነት ውሳኔና ከእሥራት የተለቀቀ ጋዜጠኛ አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 14.06.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የጥፋተኝነት ውሳኔና ከእሥራት የተለቀቀ ጋዜጠኛ አስተያየት

የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት በሰላሳ ስምንት ተቃዋሚዎች ላይ ባለፈው ሰኞ ያሳለፈውን የጥፋተኝነት ውሳኔ መንስዔ በማድረግ አርያም ተክሌ ከግንቦት 97 ምርጫ በኋላ በተፈጠረው ውዝግብ ሰበብ ታስሮ የነበረውንና አሁን ተለቆ በስደት የሚኖረውን የሳምንታዊው ጋዜጣ « አዲስ ዜና » አሳታሚና ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለምን በውሳኔው ዙርያ ባነጋገረችው ጊዜ ለምን እንደታሰረ ጠይቃው ነበር።