ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጸሙ ያሉትን ግድያዎች ገለልተኛ አካል ጣልቃ ገብቶ በማጥናት ይፋ እንዲያወጣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባት (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንገር (ኦፌኮ) ጠየቁ።
በኤስኦኤስ የህጻናት ማሳደጊያ መንደር መስራች ሔርማን ገማይነር ስም የተሰየመው የዕርዳታ ድርጅት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች አራት ሚሊዮን ዩሮ መደበ። ገንዘቡ በኤስኦኤስ ኢትዮጵያ በኩል በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ማኅበረሰቦች ለመደገፍ ይውላል።
በአፋር ክልል በተደጋጋሚ በተስተዋለው ጦርነትና ድርቅ ሳቢያ በምግብ እጥረት ወደ ሆስፒታል ከገቡ ህጻናት ከ30 በላይ የሚሆኑት ህይወታቸው ማለፉን ሆስፒታሉ አስታወቀ፡፡ ባለፉት ጢቂት ወራት በምግብ እጥረትና በሌሎች ህመሞች ወደ ዱብቲ ሪፌራል ሆስፒታል የሚመጡ ታካሚዎች ቁጥር ከሆስፒታሉ አቅም በላይ ሆንዋል ተብሎአል።
የትግራይ፣ የአማራ፣ የአፋርን ሕዝብ የፈጀዉ --- ጦርነት፣ መተከልን ያንገረገበዉ ግድያ፣ሰሜን ሸዋን ያነፈረዉ ጥቃት ገለል-ቀለል ማለቱ አስገምግሞ ሳበቃ ደዋ ጨፋ ላይ የተዋለዉ ዘግናኝ ግፍ ፈጋ።ሰሞኑን ጋምቤላ፣ዴምቢዶሎ፣ ጊምቢ ላይ የረገፈዉ አስከሬን ሲቆጠር፣የክሳይ ንዳጅ አመድ ሲዛቅ ጊምቢ መዳረሻ ዳግም ተንፈቀፈቀች።