ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የምሥራቅ አፍሪቃ ተጠንቀቅ ኃይል በእንግሊዝኛ ምህፃሩ (EASF) የፊታችን ሰኞ ሰኔ 14 ቀን፣ 2013 ዓ.ም የሚደረገውን የኢትዮጵያ ምርጫ የሚከታተሉ 28 ታዛቢዎቹን ዛሬ በይፋ ወደ ሥራ አሰማራ። ኃይሉ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዐሥር አባል ሃገራት አሉት። ነገር ግን የሰኞውን ምርጫ የሚከታተሉ ታዛቢዎች የተውጣጡት ከስምንቱ ሃገራት ነው።
የጤና ሚኒስቴር በጦርነት ከፍተኛ ውድመት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት ለማቋቋምና መልሶ ሥራ ለማስጀመር ሁሉን-አቀፍ የድጋፍ ጥሪ አቅርቧል። በዚህ መሠረትም ከአዲስ አበባ የተለያዩ ሆስፒታሎች ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች በመገኘት ሀኪም ቤቶቹ ለኅብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ለመደገፍ ተሰማርተዋል።