ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች ማኅበር መንግሥት ለመገናኛ ብዙኀን ችግሮች መፍትሄ እንዲሰጥ ለጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ደብዳቤ ላከ። ማኅበሩ የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች ከቤታቸውና ከሥራ ገበታቸው በጸጥታ ኃይሎች መታፈናቸው እንዳሳሰበው፤ ጠ/ሚሩ ይህን ከፍተኛ የሕግ ጥሰት ሰምተው እንዳልሰሙ መሆናቸው እንዳሳዘነዉ ለጠ/ሚሩ ደብዳቤ ፅፎአል።
አውሮጳ ከሩሲያ በነዳጅና በጋዝ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለማቆም እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። የደቡብ አፍሪቃዊትዋ ሀገር ናሚቢያ በነዳጁ ዘርፍ አዉሮጳን መርዳት እችላለሁ እያለች ነዉ። ናሚቢያ ይህን ያሳወቀችዉ ባለፈው ሳምንት ዳቮስ ስዊዘርላንድ ላይ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ዓመታዊ የኤኮኖሚ መድረክ ነዉ።
ከቅርብ ግዚያት ወዲህ እየተበራከተ የመጣው የግለሰቦች የሰባዊ መብት ጥሰት እንዳሳሰበው ኢሰመጉ አታወቀ። ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ግለሰቦች ከየቦታው ተጠልፈዉ ለተውሰኑ ቀናት የት እንደደረሱ አለመታወቁ እና ኃለፊነቱን የሚወስድ አካል አለመኖሩ ከፍተኛ የሰባዊ መብት ጥሰት ብቻ ሳይሆን የግለሰቦችን ህገ-መንግስታዊ መብትን መቃወም ነው ብልዋል።
በሰላም እጦት ፣ በግጭት፣ በድርቅ እና በውጭ ምንዛሪ እጥረት እየፈተነ ያለው የኢትዮጵያ የግብርና ክፍል ኢኮኖሚ ከእነ ችግሮቹም ቢሆን የምርት እድገት ያልተለየው መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ተናገረ። ሚኒስቴሩ ይህ ዘገባ የትግራይ ክልልን እንደማይጨምር አውስቷል።