የጥራት ጥያቄ ያስነሳው ጭንብል በጀርመን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 10.06.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የጥራት ጥያቄ ያስነሳው ጭንብል በጀርመን

ጀርመን ውስጥ ደረጃውን ያልጠበቀ ነው በተባለ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ምክንያት የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር እየተወቀሱ ነው። በዚህም ምክንያት የጀርመን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቡንደስታኽ በዛሬው ዕለት በጉዳዩ ላይ ተነጋግሯል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:49

ምክር ቤት አጣሪ ኮሚቴ እንዲሰየም ወስኗል

ጀርመን ውስጥ ደረጃውን ያልጠበቀ ነው በተባለ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ምክንያት የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር እየተወቀሱ ነው። ከቻይና በገፍ የተገዛው FFP2 የተሰኘው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በተለይ በኑሮ ደረጃቸው ዝቅ ላለው የኅብረተሰብ ክፍል እና ለአካል ጉዳተኞች ይሰጥ መባሉ ውዝግብ ቀስቅሷል። ሆኖም የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር የን ሽፓን ወቀሳውን በማጣጣል የተጠቀሰው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አስቀድሞ የጥራት ይዘቱ ተፈትሾ መገዛቱን ይናገራሉ። በዚህም ምክንያት የጀርመን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቡንደስታኽ በዛሬው ዕለቱ በጉዳዩ ላይ ተነጋግሮ አጣሪ ኮሚቴ እንዲቋቋም ወስኗል። ሽፓን ከሶሻል ዴሞክራት ጋር በመጣመር ሀገር የሚያስተዳድረው የመራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ፓርቲ የክርስቲያን ዴሞክራት አባል ሲሆኑ፤ ይኽ ውዝግብ በጥምረቱ መካከል ተጨማሪ የመነታረኪያ ምክንያት እንደሆነ ነው የሚነገረው።

ይልማ ኃይለ ሚካኤልን

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች