የጥረት ኮርፖሬት የቀድሞ ሥራ አስፈፃሚ እንዲፈቱ በዋግኽምራ ሰልፍ ተጠየቀ | ኢትዮጵያ | DW | 14.03.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጥረት ኮርፖሬት የቀድሞ ሥራ አስፈፃሚ እንዲፈቱ በዋግኽምራ ሰልፍ ተጠየቀ

የቀድሞው የጥረት ኮርፖሬት ሥራ አስፈፃሚ አቶ ምትኩ በየነ ከእስር እንዲፈቱ የሚጠይቅ ሰልፍ በአማራ ክልል በዋግኸምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ ተካሔደ። አቶ ምትኩ ክልሉን የሚያስተዳድረው ፓርቲ ንብረት የነበረው ጥረት ኮርፖሬትን በሥራ አስፈፃሚነት ሲመሩ ባልተገባ መንገድ የኮርፖሬሽኑ ገንዘብ እንዲባክን አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው በእስር ላይ ይገኛሉ። 

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:28

ሰልፉ የተካሔደው በሰቆጣ ከተማ ነው

“ፍትህ ለምትኩ በየነ” የሚል ሰልፍ ዛሬ በሰቆጣ ከተማ መካሄዱን የዞኑ ኮመዙኒኬሽን መምሪያ አስታውቋል፡፡ አቶ ምትኩ በየነ፣ በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብየረሰብ ዞን በተለያዩ የስራ መስኮች የሰሩ ሲሆን ዞኑን በዋና አስተዳዳሪነትም ለብዙ ዓመታት መርተዋል፡፡

በጨረሻም በጥረት ኮርፖሬት የአምባሰል ንግድ ሥራዎች ድርጅት ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ ከሌሎች ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው ተጠርጥረው  በባህር ዳር ማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታዬ ይገኛል፡፡

ግለሰቡ አፋጣኝ ፍትህ እንዲያገኝ በሚል ዛሬ በሰቆጣ ከተማ ሰልፍ መካሄዱን የዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ባለሙያ አቶ መብራቱ መኮንን ለዶይቼ ቬለ በስልክ ተናግረዋል፡፡

ሰልፈኞች ከያዟቸው መልእክቶች መከከል “ፍትህ ለምትኩ በየነ”፣ “አገራዊ ለውጡን እንደግፋለን”፣  ምትኩ በየነ ባህላችንም ልማታችንም ነው  የሚሉ መልዕክቶች መስተጋባታቸውንም አመልተዋል፡፡

Äthiopien Mitiku Beyene

አቶ ምትኩ በየነ

ከሰልፉ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ጌታቸው አሰፋ በስልክ  እንደገለፁት “ግለሰቡ ከአንድ ዓመት በላይ በማረሚ ቤት ፍትህ አላገኘም አሁንም ፍትህ ሊያገኝ ይገባል” ብለዋል፡፡

አቶ ከደር አዳነ የተባሉ ሌላው የሰልፉ ተሳታፊ በበኩላቸው በሰልፉ ከሁሉም አካባቢዎች የተወከሉ ነዋሪዎች  በሰልፉ መገኘቱንና እርሳቸውም ሰልፉን ደግፈው መውጣታቸውን አስረድተዋል፡፡

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተገኙት የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አሸብር ግርማ ህዝብ የጠቀውን ጥያቄ ለሚመለከተው አካል እንደሚያደርሱ በሰልፉ ላይ ባስተላለፉት መልእክት መግለፃቸውን ከዞኑ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መመሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ሰለፉ አንዲደረግ መጋቢት 1 ቀን 2012 ዓ ም በከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ በተፃፈ ደብዳቤ የተፈቀደ መሆኑን ዶይቼ ቬለ ማረጋገጥ ችሏል፡፡

ዓለምነው መኮንን

እሸቴ በቀለ

 

Audios and videos on the topic