የጥረት ኮርፖሬት አመራር ጉዳይ | ኢትዮጵያ | DW | 05.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጥረት ኮርፖሬት አመራር ጉዳይ

የአማራ ክልል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በጥረት ኮርፖሬት አመራር በነበሩት በአቶ ምትኩ በየነ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ምርመራ ማጠናቀቁን አስታወቀ። አቃቤ ሕግ በበኩሉ ክስ ለመመስረት የሚያስችለውን የ15 ቀናት ጊዜ ጠይቋል። ችሎቱ የግራ ቀኙን የክርክር ጭብጥ ተመልክቶ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:04

«ክስ ለመመስረት ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ተቀጠረ»

በጥረት ኮርፖሬት አመራር ሆነው ሲሰሩ ባልተገባ መንገድ የኮርፖሬሽኑን ገንዘብ እንዲባክን አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩት አቶ ምትኩ በየነ ለሶስት ጊዚያት ባባህርዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው በተጠረጠሩበት ጉዳይ የአማራ ክልል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን የተለያዩ ምርመራዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ዛሬ የአማራ ክልል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ባለፉት 14 ቀናት የደረሰበትን የምርመራ ሂደት ፍርድ ቤቱ አዳምጧል፡፡ መርማሪ ቡድኑም «ምርመራየን አጠናቅቂለሁ ክስ የመመስረቻ ጊዜ የ15 ቀናት ቀጠሮ ይሰጠኝ» ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡ የአቶ ምትኩ በየነ ጠበቃ በበኩላቸው ደንበናቸው የተጠረጠሩበት ወንጀል የተፈፀመው በ2005 ዓ ም በመሆኑ፣ የተጠየቀው ክስ የመመስረቻ ጊዜም ረጅምና ደንበኛቸው በመኪና አደጋ ክፉኛ የተጎዱ፣ ያለስራና ያለደመወዝ ቤተሰብ ስለሚያስተዳድሩ ጭምር የተጠረጠሩበት ጉዳይም ዋስትና ስለማይከለክል ዋስትናቸው ይጠበቅ ሲሉ ተከራክሯል፡፡

የአማራ ክልል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን በበኩሉ የተሰበሰቡ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች በርካታ ስለሆኑ ቀኑን ማሳጠርም ሆነ ዋስትና መስጠት ተገቢ እንዳልሆነ ተከራክሯል፡፡ ጤናቸውን በተመለከተ ግን ኮሚሽኑ አስተያየት መስጠት አልችልም ነው ያለው መርማሪ ቡድኑ፡፡

የባሕር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን አሰተያየት መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ 8 ሰዓት ቀጠሮ ይዟል። አቶ ምትኩ በየነ የጥረት ኮርፖሬት ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ሢሠሩ በ2005 ዓም በየዳ ለተባለ አክሲዮን ማህበር 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ያላግባብ የአክሲዮን ግዥ ከጥረት ኮርፖሬት እንዲከፈል አድርዋል።

እንዲሁም ለባህርዳር ሞተርስ አክሲዮን ማህበርና ለበየዳ ሳስተነብል አክሲዮን ማህበራት ከህግ ውጪ ከሌሎች አመራሮች ጋር በመሆን የ4 ነጥብ 65  ሚሊዮን ብር ብድር ፈቅደዋል በሚል ተጠርጥረው ጉዳያቸው ፍርድ ቤት ቀርቦ በአማራ ክልል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ሲታ ቆይቷል፡፡ የአማራ ክልል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ጥረት ኮርፖሬትን ለኪሳራ ዳርገዋል በሚል የቀድሞዎቹን የኮርፖሬሽኑን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ በረከት ስምዖንነና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ካሳን በሕግ ቁጥጥር ስር አውሎ ጉዳያቸውን እየመረመረ መሆኑ ይታወሳል።

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ተስፋለም ወልደየስ

Audios and videos on the topic