የጥረት ኮርፖሬሽን ም/ሃላፊ ክስ ለሰኞ ተቀጠረ | ኢትዮጵያ | DW | 01.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጥረት ኮርፖሬሽን ም/ሃላፊ ክስ ለሰኞ ተቀጠረ

የባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛው ፍርድ ቤት አቶ ምትኩ በየነ ለሰኞ ከሰዓት እንዲቀርቡ  የወሰነው የባህርዳሩ ወኪላችን አለምነው መኮንን እንደዘገበው በጊዜ መጣበብ ምክንያት ነው። ሆኖም ፍርድ ቤቱ የቀሪ አራት ተጠረጣሪዎችን ጉዳይ ዛሬ ተመልክቷል።

የጥረት ኮርፖሬሽንን ላልተገባ ወጪ ዳርገዋል የተባሉት የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ምትኩ በየነ ተከስሰው ዛሬ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ጉዳያቸው የፊታችን ሰኞ  እንዲታይ ተወስኗል። ዛሬ ጉዳያቸውን ሊመለከት የነበረው የባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለሰኞ ከሰዓት እንዲቀርቡ  የወሰነው የባህርዳሩ ወኪላችን አለምነው መኮንን እንደዘገበው በጊዜ መጣበብ ምክንያት ነው። ሆኖም ፍርድ ቤቱ የቀሪ አራት ተጠረጣሪዎችን ጉዳይ ዛሬ ተመልክቷል። ዝርዝሩን ካባህርዳር አለምነው መኮንን ልኮልናል። 
አለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic