የጥምቀት በአል ባህላዊዉ ወጉና ፍችዉ | ባህል | DW | 24.01.2010
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ባህል

የጥምቀት በአል ባህላዊዉ ወጉና ፍችዉ

ያሁኑ ኩራት ለምንድን ነዉ፣ ያሁኑ ኩራት ለምንድን ነዉ፣ ሁሉም የተሰራዉ ላፈር ነዉ!እሱ አይደለም ወይ ባለቤቱ፣ እሱ አይደለም ወይ ባለቤቱ፣ ቀጭን ኩታ ለብሶ ምንድ ነዉ ኩራቱ!

default

በኢትዮጽያችን የጥምቀት በአልሲከበር፣ ታቦት ሲወጣ ህዝብ በዜማዉ በጭፈራዉ መሳተፍ አለበት ሲልያገሪ ሰዉ ግጥም እየደረደረ የበአሉን ታዳሚ እንዲያዜም እልልእንዲልያደርጋል። በጥምቀት መነኩሴዋ ሳይቀሩ ታቦት በሚወጣ ቀን በምስጋና ያዜማሉበሽብሸባዉ ላይ ይሳተፋሉ። የጥምቀትን በአልያላከበረ ታቦት ያልሸኘም ይወረፋል፣ በዜማ በግጥም ይነቀፋል!

ዳቢሎሽ ሞተ አሉከነሚስቱ፣ ዳቢሉስ ሞተ አሉከነሚስቱ፣ ተስካሩን ያዉጡለት ከዚህ ያልመጡቱ! ይለዋል። ጤና ይስጥልኝ አድማጮች! በዛሪዉ ጥንቅር የጥምቀት በአልን በማስመልከት የአከባበር ስነ-ስርአቱን በባህሉያለዉን ወግልናወጋ ይዘናል፣ ለጥንቅሩ አዜብ ታደሰ ነኝ መልካም ቆይታ።

በጥምቀት ህጻን አዋቂዉ አዲስ ልብስ ለብሶ ገንዘብ የሌለዉም፣ ያለዉን በንህጽና አጥቦ ለብሶ በአሉን ለማክበር ይዘጋጃል። በጥምቀት ታቦት ማንገሱ ከሃይማኖት ሌላ የጥምቀት መድረክ ፍቅረኛ ማግኛም ነዉ። እንደዉም ለጥምቀት በአልያልዘፈነች ቆንጆ፣ ቆማ ትቀራለች እንደዘላን ጎጆ! ይባላል። የጥምቀት በአልፍችዉ ምን ይሆን፣ መኖርያቸዉ በአሜሪካ ሎሳንጀለስ ነዉ፣ የጥምቀትን በአልፍች እንዲነግሩን ፈልጌ ያገኘኻቸዉ ደቡብ አፍሪቃ፣ ጆሃንስበርግላይ ነዉ። አባቴ እስቲ ስለ ጥምቀት ያስረዱኝ ስልጠየኻቸዉ። አባ ወልደ ትንስኤ ይባላሉ፣ ሰፋ ያለ ትንተና ሰጥተዉናል፣ ያድምጡ! በተጨማሪ በጥምቀት በአልላይ ያልጨፈረ፣ ያላጨበጨበ ይወረፋል። እማሆይ ሳይቀሩ ካላጨበጨቡ ይወረፋሉ። ምነዋ እማሆይ ዝም አልሽ፣ ምነዋ እማሆይ ዝም አልሽ፣ ዋንጫ ጠላ ቦሆን፣ አይለፈኝ ባልሽ፣ ጠላዉማ ቢሆን ይበቃልባላልሽ! ሲባልይተቻሉ።

Orthodoxe Christen in Äthiopien

መነኩሲትዋ ብዙ ግዜ በቤተስኪያን ጥገኛ ሆነዉ ምግብ እና ጠላን ስለሚያገኙ ነዉ። ለጠላዉ ሲሆን ማንም አልቀደመሽ፣ ለታቦቱ ምስጋና ግን ወደ ኻላ ቀሩ ለማለት። ሌላም አለ! ኸረ ተይ እማሆይ ተነሽ፣ ኸረ ተይ እማሆይ ተነሽ፣ መድሃንያለም ቆሞ ምነዋ ዝም አልሽ፣ እየተባለ ይዜማል፣ ይዘመራል። እማሆይ በዚህን ግዜ ምስጋናቸዉን ለማሳየት ቆባቸዉን እንዳደረጉነጠላቸዉን ወገባጨዉ ላይ ሸብ አድርገዉ፣ አንገታቸዉን ሰበቅ ሰበቅ በማድረግ፣ ይወዛወዛሉ፣ ያጨበጭባሉ፣ ከዝያም የጥምቀት በአልእድም ተኛ እማሆይን ሊያመሰግን ይነሳል፣ እማሆይ ባለ አበባ እማሆይ ባለ አበባ፣ ከላይ ቆብ ከታች ዳባ! ሲባልይሞገሳሉ። በሌላ በኩልገበያ ያልመጣች ሴት እንዲህ ትወቀሳለች፣ መልካም ገበያ ቀረብሽ፣ መልካም ገበያ ቀረብሽ፣ ቡናዉና ቁርሱ ይቀራልብለሽ፣ ያ የማለዳ ፍትፍት ይቀራልብለሽ። ወይ እንደኔ ማልደሽ በመጣሽ! ትባላለች። ለጥምቀት ያልመጣዉም ወንድ እንዲሁ ይወረፋል፣ ከቤት ይዉላልሞኙ፣ ከቤት ይዉላልሞኙ፣ እናት እና ልጁ በጥምቀት ሲገኙ!

መልካም ገበያ ገበይን፣ መልካም ገበያ ገበየን፣ እናት እና ልጁን፣ በአንድ ላይ አየን፣ አለቀሰ አሉዳቢሎስ፣ አለቀሰ አሉዳቢሎስ፣ ትንሹ ትልቁ፣ ግሸን ላይ ሲደርስ፣ አሞራ በሰማይ ሲያይህ ዋለ፣ አሞራ በሰማይ ሲያይህ ዋለ፣ የጊዮርጉስ ናት እያለ፣ የተክልዪ ናት እያለ፣ ይባላልታቦቱን የሚንከባከቡት ቀሳዉስትም እንዲ ሲባልይመሰገናሉ። የአገራችን መምህር ቅኔዉ ሲያምር፣ የአገራችን ደብተራ ቅኔ ሲመራ! መመቀጠል ያድምጡ!

 • ቀን 24.01.2010
 • አዘጋጅ Azeb Tadesse
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/LfRl

ተዛማጅ ዘገባዎች

 • ቀን 24.01.2010
 • አዘጋጅ Azeb Tadesse
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/LfRl