የጥላሁን ገሠሠ ሥራዎችና አዳዲሶቹ ከያንያን | ባህል | DW | 15.08.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የጥላሁን ገሠሠ ሥራዎችና አዳዲሶቹ ከያንያን

ጥበብ በፀጋዋ የተላበሰችዉ ሙዚቃ አቅፋ ያሳደገችዉ ዕንቁ የሙዚቃ አባት ጥላሁን ገሰሰ ለ53 ዓመታት በዘለቀው የመድረክ ቆይታው በሙዚቃ አፍቃሪዎች ዘንድ ልዩ ጣዕም ባላቸው ሙዚቃዎቹ፤ ዘላለማዊ የሆነ ስምን ተክሎ አልፎአል ።

ጥላሁን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ በምስራቅ አፍሪካ እጅግ ተወዳጅ ታላቅ የሙዚቃ ሰው እንደሆን ያታወቃል።
የዕለቱ ዝግጅታችን ትኩረት እዉቁ የሙዚቃ ንጉስ ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ አይደለም ። ከዚያ ይልቅ ትኩረታችን አዳዲሶቹ የኢትዮጵያ ከያኒዎች የአንጋፋ ከያንያንን የጥበብ መንገድ በመያዝ በተለይ ደግሞ የጥላሁንን ዘፈኖች የሚጫወቱ ወጣት ሙዚቀኞች ብቅ ማለታቸዉ እየተበራከተ መምጣቱ ነዉ። እዉነታዉ በስራዉ ህያዉ የሆነዉ የዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ሙዚቃዎች በአሁኑ ትዉልድ መዜማቸዉ የጥላሁን ገሠሠ ሥራዎችና አዳዲሶቹ ከያንያንወቅት በግብዣ ወደ ለንደን የመጣ ሙዚቀኛን በእንግድነት ይዘናል፤ አንጋፋ ሙዚቀኞችስ የሙዚቃ ስራዎቻቸዉ በአዲሱ ትዉልድ ከያኒዎች ሲዘፈን ሲያዩ ምን ይላሉ ብለን ከያኒ አለማየሁ እሸቴን፤ እንዲሁም ፀሃፊ ተዉኔት ጌታቸዉ ደባልቄን በምሽቱ ቅንብር እንግዶቻቸችን አድርገናል።


የባህል ሙዚቃ ያደገበት እ ንደሆን ይናገራል ግን የጥላሁንን ሙዚቃዎች ሲያዜም በርካቶችን በማስደመሙ አስተማሪዉ ፤ በሙዚቃ እንዲቀጥል ስለመከሩት ፤ በኪነ-ጥበቡ ዘርፍ ገፋሁበት ይላል ሙዚቀኛ አራጋዉ ዓለሙ ። የጥላሁንን ሙዚቃ ጥሩ አርጎ በማዜሙም በእንግድነት ወደ ለንድን እንደመጣ ይናገራል ። አራጋው በተለያዩ አገራት እየተዘዋወረ የጥላሁንን ድምፅ አስመስሎ ይዘፍናል ።

አዜብ ታደሰ
ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic