የጤና ባለሞያዎች የተቃውሞ ሰልፍ በባሕር ዳር | ኢትዮጵያ | DW | 25.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጤና ባለሞያዎች የተቃውሞ ሰልፍ በባሕር ዳር

የጤና ባለሙያዎችና የስፔሻላይድ ህክምና ተማሪዎች ጥቅማጥቅም እና ደሞዛቸው እንዲስተካከል ዛሬ ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ በአደባባይ ሠልፍ ጠየቁ። ሰልፈኞቹ በዋነኛነት ተገቢ ደሞዝ እንደማይከፈላቸው ተናግረዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:28

ሰልፈኞቹ ተመጣጣኝ ደሞዝ እንደማይከፈላቸው ተናግረዋል

የጤና ባለሙያዎችና የስፔሻላይድ ህክምና ተማሪዎች ጥቅማጥቅም እና ደሞዛቸው እንዲስተካከል ዛሬ ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ በአደባባይ ሠልፍ ጠየቁ። ሰልፈኞቹ በዋነኛነት ተገቢ ደሞዝ እንደማይከፈላቸው ተናግረዋል። እንደ አብነትም አዲስ አበባ ላይ የተቀጠሩ ሐኪሞች በሚያገኙት ወርሃዊ ደሞዝ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማለትም ኮንዶሚኒየም እንኳን መከራየት አልቻሉም ሲሉ አማረዋል። የሐኪም እጥረት ባለባት ሀገር በርካታ ሐኪሞች ሥራ አጥ መኾናቸውም አግባብ አለመኾኑን ገልጠዋል። በሞያው ባልሰለጠኑ፤ ህክምናውን በማያውቊ ለፖለቲካ መሪዎች ታዛዥነታቸው በተረጋገጡ ሰዎች መመራታቸው እንደተቸገሩም ገልጠዋል። 

በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችና የስፔሻላይድ ህክምና ተማሪዎች የጥቅማጥቅም አልተጠበቀልንም በሚል ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ፡፡ የክልሉ ጤና ቢሮ ደግሞ ጉዳዩ እኔን አይመለከትም ብሏል፡፡

ከአራት ሆስፒታሎች የተውጣጡ 200 የሚሆኑ ሐኪሞችና ና ሰፕቺሊዝድ ተማሪዎች ለምንጠይቃቸው ጥያቄያች መንግስት አፋጣኝ መልስ አልሰጠንም ብለዋል፡፡ ከሰልፈኞቹ መካከል አንዳንዶችን አነጋግረን የቅሬታቸውን ምክንያት ነግረውናል፡፡ በተጨማሪም ከፍተኛ ታካሚ ባለበት አገር በርካታ ሀኪሞች ያለስራ መቀመጣቸውን ተናግረዋል፡፡

ሌላው ባለሙያደግሞ ሙያዉን በማያውቁ ሰዎች ተቋማቱ ስለሚመሩ ሙያው ወድቋል ይላሉ፡፡ ሚዲዎችን ጨምሮ ሌሎች ተፀዕኖ ፈጣሪዎች ለስራችንም ሆነ ለችግራችን ትኩረት እየሰጡን አይደለም ብለዋል ዛሬ  በባህር ዳር በሰልፍ ቅሬታቸውን ያሰሙ ሐኪሞች፡፡ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አበባው ገበየሁ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተለማማጅ ሐኪሞች በመሆናቸው ጉዳዩ አይመለከተኝም ብለዋል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች