የጣይቱ ሆቴል የእሳት ቃጠሎ | ኢትዮጵያ | DW | 11.01.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጣይቱ ሆቴል የእሳት ቃጠሎ

እቴጌ ጣይቱ ሆቴል የመጀመሪያው ዘመናዊ የኢትዮጵያ ሆቴል ሲሆን የተመሰረተው እ.ኢ.አ. በ ነሐሴ 1898 ዓ.ም ነበር። ይህ ሆቴል ዛሬ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ደረሰበት

ሆቴሉን ዳግማዊ አጼ ምኒሊክ ጥቅምት 25 ቀን 1900 .. በአዲስ አበባ የሚገኙ የውጭ ሃገር ዲፕሎማቶችን በመጋበዝ እንዳስመረቁት ጳውሎስ ኞኞአጤ ምኒልክበተሰኘ መጽሃፋቸው ገልጸዋል። ሆቴሉ ስራ በጀመረበት ዘመን የሆቴል ስራ ኢትዮጵያ ውስጥ የተለመደ ባለመሆኑ ከፍተኛ የገበያ ችግር ገጥሞት ነበር። ንጉሱ አጼ ምኒሊክ መኳንንቱን በተደጋጋሚ በመጋበዝ ሆቴሉና አገልግሎቱ እንዲለመድ ማድረጋቸውን ጳውሎስ ኞኞ በመጽሃፋቸው አስፍረዋል።

የጣይቱ ሆቴል ታድሶ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ በኃላ በታሪኩና በሚያቀርበው የጃዝ ሙዚቃ በተለይ በውጭ ሃገር ዜጎች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቶ ነበር።

ይህ ሆቴል ዛሬ የእሳት አደጋ እንደገጠመው ተሰምቷል። ስለደረሰው አደጋ የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ዮሀንስ ገብረ እግዚያብሄር ።

ዮሀንስ ገብረ እግዚያብሄር

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic