የጠ/ሚ ጽ/ቤት መግለጫ በወቅታዊ ጉዳዮች | ኢትዮጵያ | DW | 18.08.2022
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጠ/ሚ ጽ/ቤት መግለጫ በወቅታዊ ጉዳዮች

መንግሥት በትግራይ ክልል የመሠረታዊ አገልግሎቶች እንዲመለሱ በየትኛውም ጊዜ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለውይይት ዝግጁ መሆኑን እንዲሁም ጦርነትን በዘላቂነት ለማስቀረት የተከስ አቁም እንዲደረግ እቅድ መያዙን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ገለፀ።

የጠ/ሚ ጽ/ቤት መግለጫ በወቅታዊ ጉዳዮች

መንግሥት በትግራይ ክልል የመሠረታዊ አገልግሎቶች እንዲመለሱ በየትኛውም ጊዜ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለውይይት ዝግጁ መሆኑን እንዲሁም ጦርነትን በዘላቂነት ለማስቀረት የተከስ አቁም እንዲደረግ እቅድ መያዙን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ገለፀ። የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ዛሬ ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በሰጠው መግለጫ መንግሥት ቅድሚያ የሚሰጠውን ብሔራዊ የሰላምና ደኅንነት ጉዳይ የተመለከቱ ሥራዎች በፀጥታ ተቋማት ተጠናክሮ ሲያከናወን ቆይቷል ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ሥዩም የቀረበው ማብራሪያ ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮችንም ዳሷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ሥዩም "መንግሥት በትግራይ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለመጀመር  በክልሉ መንቀሳቀስ መቻልን ፣ በክልሉ የሚገኙ ልዩ ልዩ መሥሪያ ቤቶችን ማንቀሳቀስ መቻልን እና ከሌላኛው ወገን ጋር ሰላማዊ ግንኙነትና ንግግር ይጠይቃል" ብለዋል። 

"ሕወሓት ጥቃት ከፍቶ በነበረበት ወቅት ውድመት ከማድረሱ ባሻገር ማኅተምን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት ንብረቶችን ዘርፎ ስለነበር ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አባባ ይገቡ በነበሩ ዜጎች ላይ የጉዞ እገዳ ተጥሎ የነበረው ሀሰተኛ መታወቂያዎችን ለማምክን እና በዋና ከተማ አዲስ አበባ ለመፍጠር ታስቦ የነበረን የፀጥታ ስጋት ለመቀልበስ ነው" በማለት ችግሩ እንደነበር አምነው አሁን እንደተፈታ እምነታቸው መሆኑን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያን ሰላምና ደኅንነት ሰፋ አድርጎ በተመለከተው የዛሬው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መግለጫ በኦሮሚያ ክልል የሽብር እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል በተቋቋሙ ሦስት ግብረ ኃይሎች፣ በፌዴራል እና በክልል መንግሥታት የጋራ የፀጥታ ኃይሎች ስምሪት ጥምረት ቁልፍ የሚባሉ እና የሽብር ቡድን ሕዋስ አባል የሆኑ ሰዎችን እስከመያዝ የደረሱ ተግባራት መፈፀማቸው ተገልጿል።

በአማራ ክልል ኢ - መደበኛ በተባሉ ኃይላት ላይ ሕግ የማስከበር ሥራዎች ውጤት ማስገኘታቸውን እና አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች ክልሎችም የጥፋት የተባሉ ኃይሎችን በመያዝ ፣ ጥቃቶችን በመቀልበስ እና የፀጥታ ተቋማትን በማፅዳት ረገድ የተሻለ ሥራ መከናወኑን የፀጥታና ደኅንነት ምክር ቤቱን መግለጫ አስታውሰው ቢልለኔ ሥዩም ገልጸዋል። 

የጸጥታ እና ደኅንነት ምክር ቤቱ የሽብር ኃይሎችን እና ኢ መደበኛ ኃይሎችን አቅም ለማዳከም እና ሥጋት መሆን የማይችሉበት ደረጃ ላይ እስኪደርሱ ድረስ የተጀመሩ ዘመቻዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ትዕዛዝ ማስተላለፉን አስታውሰዋል። ምክር ቤቱ የሕግ ተቋማት ለብሔራዊ ሰላም እና ደኅንነት የሚያስፈልገውን ሁሉ መፈፀም እንዲችሉ እንዲሁም በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ የሚፈፀሙ አሻጥሮች ፣ በሙስና እና ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀሎች ላይ በሚሳተፉት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወስዱ ፣ በሁሉም የፀጥታ ተቋማት ውስጥ በየትኛውም ደረጃ ያሉ አመራሮች እንዲፈተሹ ብሎም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ትእዛዝ መተላለፉን አስታውቀዋል። 

የፌዴራል የሰላም አማራጭ አቢይ ኮሚቴ በትግራይ መሰረታዊ ግልጋሎቶችን ለማስጀመር ንግግር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲጀመር አቅጣጫ ማስቀመጡንና "ትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ለሕወሓት የፖለቲካ ፍላጎት ሲባል እሥረኞቹ ሊሆኑ አይገባም"  የሚለው የመንግሥት ውሳኔ መነሻ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የሰላም አማራጭ አቢይ ኮሚቴ "በሚቀጥለው ሳምንት የተኩስ አቁም ለማድረግ የሰላም ንግግር እንዲደረግ እቅድ ይዟል። በመቀጠል ወደ ሰላም ድርድሩ መመቻቸት የሚመራ ጥልቅ የፖለቲካ ውይይት በሁለቱ አካላት መካከል ለማድረግ አቅዷል።

ሦስተኛ ሌሎች ያልተፈቱ ቀሪ ጉዳዮች በብሔራዊ ምክክሩ እንዲፈቱ እቅድ ይዟል። ይህ የሰላም አቢይ ኮሚቴው እቅድ የፌዴራል መንግሥቱ ግጭቱን በሰላም ለመፍታት እና ለሰላም ያለው ያልተቋረጠ ቁርጠኝነት ሌላኛው ማሳያ ነው" ብለዋል። መንግሥት የተኩስ አቁም ለማድረግ የሰላም አማራጭ አቢይ ኮሚቴው ከዛሬ ጀምሮ ጉዳዩን ላይ ተቀምጦ ለመነጋገር እና ችግሩን በንግግር ለምፍታት ፈቃደኝነቱን ማሳወቁን ገልፀዋል። ለሰላም ማነቆ የሆነው ማነው የሚለው በሁሉም ወገኖች መፈተሽ እንዳለበት እና አገልግሎቶቹ እንዳይመለሱ እንቅፋት የሆነው ማነው የሚለው ሊታይ ይገባልም ብለዋል። በሕወሓት በኩል አሁንም ጦር የመስበቅ፣ የጦርነት መሻት እና ስጋት የመፍጠር ፍላጎት ይታያልም ብለዋል። የተኩስ አቁም የሚለው የውሳኔ ሀሳብ ለመሰረታዊ አገልግሎቶች ማስጀመር የቀረበ አለመሆኑን አስታውሰዋል። 

"በትግራይ ክልል ያለውን የመሰረተ ልማት ጥገና ለማድረግና አገልግሎቶችን ለመመለስ የክልሉ የፀጥታ እና አስተዳደር ሁኔታ መስተካከልና በቦታው መገኘት አለበት የሚለውን መንግሥት ለአጋሮቹ እና ለሕዝቡ በተለያየ ሁኔታ ግልጽ አድርጓል። ስለዚህ ሥራዎችን መሬት ላይ ለማከናወን ማረጋገጫ እና አስቻይ ሁኔታዎች አስፈላጊ ናቸው።
በአሁኑ ጊዜ ግን ራሱን ያስታጠቀው ቡድን የጦር ጉሰማውን እየገለፀ ስለሆነ እና የሰላም ንግግሩንም ለመቀበል አሻፈረኝ በማለቱ አገልግሎቶችን ለመመለስ የሚፈለገው አስቻይ ሁኔታ ባለመኖሩ አገልግሎቱ ዘግይቷል። ሕወሓት በትግራይ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ደኅንነት የሚጨነቅ ከሆነ በተለያዩ ዓለም አቀፍ አካላት የሰላም አጀንዳውን እንዲቀበል እና ለሰላም ጥረቱ ምክንያት ከመፈለግ ተቆጥቦ ለሰላም ውይይቱ እንዲቀመጥ በግልጽ በአደባባይ ሊነገረው ይገባል" ብለዋል።

ሕወሓት በአማራ እና አፋር ክልሎች ላይ ጥቃት ከፍቶ በነበረበት ወቅት ውድመት ከማድረሱ ባሻገር ማኅተምን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት ንብረቶችን ዘርፎ ነበር ያሉት የጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ሥዩም ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አባባ ይገቡ በንበሩ ዜጎች ላይ እገዳ ተጥሎ የነበረው "ሀሰተኛ መታወቂያዎችን ለማምክን እና በዋና ከተማ አዲስ አበባ ላይ ለመፍጠር ታስቦ የነበረን የፀጥታ ሥጋት ለመቀልበስ ነው" በማለት ችግሩ እንደበበር እና አሁን እንደተፈታ እምነታቸው መሆኑን ገልፀዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በትግራይ ክልል ያለው የሰብዓዊ ሁኔታ የከፋ ነው ስለማለታቸው የመንግሥትን ምላሽ የተጠየቁት ኃላፊዋ ጉዳዩን የሚያስገርም እንዳልሆነና ከፍተኛ ኃላፊነት ላይ ያሉ ሌሎች ሰዎች ከሚያደርጉት ክስ አንዱ መሆኑን ገልፀው፣ የተባበሩት መንግሥታት ያለማቋረጥ በተቋሙ መሪ እየተጣሰ ያለውን የድርጅቱን የገለልተኝነት መርህ ይመለከተዋል ብለን እናስባለን "ዳይሬክተር ጀነራሉ ብሽብርተኝነት የተፈረጀውን ድርጅት ትርክት ማስተጋባታቸውን ከቀጠሉ ከዓለማቀፉ ከፍተኛ ደረጃ ያለው ኃላፊነታቸው እንዲለቁ ይመከራል" ብለዋል።

የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን በተመለከተ እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ከሀምሌ 28 እስከ ነሀሴ 9 2022 ድረስ ወደ ትግራይ 30 ሺህ ቶን የተጠጋ ምግብ ፣ 31 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች ፣ 300 ሚሊዮን ጥሬ ብር ፣ ከ66 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ ፣ 23 .6 ሜትሪክ ቶን መድኃኒት ፣ 296 ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ለሩቱ ተጠቃሚዎች እንዲሰራጭ መቀሌ  መድረሱንና በተመሳሳይ ወደ አማራ ክልል 7543 ሜትሪክ ቶን ምግብ እና 3000 ሜትሪክ ቶን የተጠጋ የምግብ አቅርቦት ወደ አፋር ክልል ተልኳል ብለዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic