የጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሕዝባዊ መድረክ ቅድመ-ዝግጅት በፍራንክፈርት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 30.10.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሕዝባዊ መድረክ ቅድመ-ዝግጅት በፍራንክፈርት

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ውልደ ኢትዮጵያውያን በነገው ዕለት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በፍራንክፈርት ከተማ በሚካሄደው ሕዝባዊ ውይይት ላይ ለመካፈል ጀርመን መግባት መጀመራቸውን የመርሃ ግብሩ አስተባባሪዎች ገለጹ::

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:01

«አንድ ሆነን እንነሳ ነገንም እንገንባ»

 " አንድ ሆነን እንነሳ ነገንም እንገንባ " በሚለው የለውጡ ኃይል መሪ ቃል በተዘጋጀው በዚሁ አውሮፓ አቀፍ ታሪካዊ ጉባኤ ኢትዮጵያውያን ዝግጅቱ ለሚከናወንበት ትልቁ የኮሜርዝ ባንክ አሬና ስታዲየም ኪራይ እና የተለያዩ ወጪዎችን ለመሸፈን የተሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ማካሄዳቸውንም በፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጄኔራል ቆንሱል አቶ ምህረተዓብ ሙሉጌታ ለ DW ገልጸዋል:: በጀርመን ነዋሪ የሆኑ ከ 200 በላይ ወጣቶች ዝግጅቱን በበጎ አገልግሎት ለማስተባበር በፈቃደኝነት የተመዘገቡ ሲሆን ከመላው አውሮፓ በመኪና ለሚመጡ ታዳሚዎችም ከ 10 ሺህ በላይ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች መዘጋጀታቸው ታውቋል ። ዝርዝሩን እንዳልካቸው ፈቃደ አጠናቅሮታል::

እንዳልካቸው ፈቃደ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች