1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠ/ሚ የአዲስ አበባ ንግግርና የሕዝብ አስተያየት 

ሰኞ፣ ሚያዝያ 8 2010

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ትናንት በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ያደረጉት ንግግር «ርቆ የተሰቀለ ዳቦ ዓይነት ነዉ» ሲሉ ለዶቼ ቬለ አስተያየታቸዉን የሰጡ የጣብያዉ ተከታታዮች ተናገሩ። ንግግሩ በበጎ ጎኑ ቢመለከቱትም በተግባራዊነቱ አብዝተዉ መጠራጠራቸዉን ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/2w9GA
Äthiopien Abiy Ahmed OPDO
ምስል Abdulbasit Abdulsemed

የጠ/ሚኒስትሩ የአዲስ አበባ ንግግርና የሕዝብ አስተያየት 


ጠ/ሚ  ዶ/ር አቢይ አህመድ በአዲስ ሚሊኒየም አዳራሽ ያደረጉት ንግግር ተስፋ ሰጭ ቢሆንም ተግባራዊነቱን ግን ብዙዎችን አጠራጥሮአል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስካሁን በጅጅጋ ፤ አንቦ መቐለ ትላንት ደግሞ በአዲስ በባ ከሕዝብ ወኪሎች ጋር ተገናኝተዉ ያደረጉዋቸዉ ንግግሮች በአብዛኛዉ ተስፋን አጭሮአል። የትናንት የአዲስ አበባ በአብዛኛዉ ወጣቶች በተገኙበት የሚሊኒየም አዳራሽ ስብሰባ ላይ ያደረጉት ንግግርም እንደከዚህ ቀደሞቹ ተስፋና ስጋትን አጭሮአል።  በኮተቤ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምሕር የሆኑት ዶ/ር ተስፋዬ ሞላ ንግግሩ በአጠቃላይ ፍትህና መልካም አስተዳደርን በማንገስ የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋትና በሌሎች አገራዊ አጀንዳዎች በአዎንታዊ መልኩ ተመልክተዉታል።
ገዥዉ ፓርቲ ከመሰረተዉ የፓርላማዊ ስርዓት አወቃቀርና ፓርቲዉ  ከሚከተለዉ የቡድን አመራር ሰጭነት አንፃር የንግግሩ ተግባራዊነት አንፃር ብዙዎችን ጥርጣሬ ዉስጥ ከቷል። ዶክተር ተስፋዬም ይህንኑን ይጋራሉ።
የድሬደዋ  ወጣት አምሃ ታደሰ በበኩሉ የጠ/ሚሩ የእሁድ ንግግር በብዙሃን መገኛኛ ከተከታተሉት ወጣቶች አንዱ ነዉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ስልጣን ከተረከቡ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እያደረጉት ያለዉ ንግግር በተስፋ ሰጭነቱ ብዙዎች በአዎንታ ቢመለከቱትም ከእሳት ማጥፋት የዘለለ ትርጉም ይኖረዉ ይሆን? በማለት ግን ስለተግባራዊነቱ ይጠራጠራሉ። 


ዮሃንስን ገብረግዚአብሄር 
አዜብ ታደሰ 
ተስፋለም ወልደየስ