የጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ የአስመር ጉብኝትና የሕዝብ አስተያየት  | ፖለቲካ | DW | 09.07.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ፖለቲካ

የጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ የአስመር ጉብኝትና የሕዝብ አስተያየት 

የኤርትራው ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ እና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አሕመድ በተለያዩ የሰላምና የወዳጅነት ግንኙነቶች ላይ የጋራ መግባብያ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 01:47
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
01:47 ደቂቃ

«ጊዜዉ የመደመር ነዉ፤ ደስ ብሎናል»


በዚህ ስምምነት ኢትዮጵያና ኤርትራ የነበሩበት ጦርነትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማብቃቱን በይፋም አዉጀዋል፤ በፊርማቸዉም አፅድቀዋል። ጠ/ሚ ዐብይ የኤርትራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ዛሬ ከቀትር በኋላ  አዲስ አበባ ገብተዋል።  ዶቼቬለ ያነጋገርናቸዉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንደሚሉት ኤርትራዉያን እና ኢትዮጵያዉያን ወንድማማች ሕዝቦች መሆናቸዉን ኤርትራዉያን አስመስክረዋል። በአስመራ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የተደረገው አቀባበል የእዚህ አንዱ ማሳያ ነዉ ብለዋል።   


ዩሐንስ ገ/እግዚአብሔር 
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic