የጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የጀርመን ጉብኝት | የመገናኛ ብዙኃን ማዕከል ሙሉ ይዘት | DW | 02.11.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የጀርመን ጉብኝት

«አንድ ሆነን እንነሳ፣ ነገንም እንገንባ» በሚል መርህ በተዘጋጀው በፍራንክፈርቱ መርሃ ግብር ላይ ዶክተር ዐብይ ከተለያዩ የአውሮጳ ሀገራት እና የጀርመን ከተሞች የመጡ ኢትዮጵያውያን በተወካዮቻቸው አማካይነት ላቀረቡላቸው ጥያቄዎችም  መልስ ሰጥተዋል። የፀጥታ ችግሮች፣የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የክልሎች የሥልጣን ገደብ፣ ከጥያቄዎቹ መካከል ይገኙበታል።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ሥልጣን ከያዙ የመጀመሪያው በሆነው የጀርመን ጉብኝታቸው ጥቅምት 20፣2011 ዓም ርዕሰ ከተማ በርሊን በተካሄደው የቡድን ሀያ ጉባኤ ላይ ከተካፈሉ በኋላ ጥቅምት 21፣2011ዓም በፍራንክፈርት «ኮሜርስ ባንክ አሬና» በተባለው ስታድዮም ለተሰበሰቡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ንግግር አድርገዋል። «አንድ ሆነን እንነሳ፣ ነገንም እንገንባ» በሚል መርህ በተዘጋጀው በፍራንክፈርቱ መርሃ ግብር ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከተለያዩ የአውሮጳ ሀገራት እና ከልዩ ልዩ የጀርመን ከተሞች የመጡ ኢትዮጵያውያን በተወካዮቻቸው አማካይነት ላቀረቡላቸው ጥያቄዎችም  መልስ ሰጥተዋል። የፀጥታ ችግሮች፣የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የክልሎች የሥልጣን ገደብ፣ የህገ መንግሥቱ አንቀጾች ማሻሻያ ፣የፌደራል ስርዓቱ ጥቅም እና ሌሎችም ለዶክተር ዐብይ ከተነሱት ጥያቄዎች ውስጥ ይገኙበታል። ዶክተር ዐብይ ከሰጡት መልስ መካከልም  «በሐገሪቱ የሕግ የበላይነት ይረጋገጣል ስለዚህም ህዝቡ ሊታገስ ይገባል፤ አሁን የሚስፈልገን አገራዊና ኢትዮጵያን ያገናዘበ አስተሳሰብ ነዉ፤ሕገ መንግስቱ ይሻሻል ለሚለዉ ጥያቄ ሕዝቡ ተወያይቶ የሚያሻሽለዉ ጉዳይ ነዉ፤ብሔራዊ እርቅ ለማድረግ ዉይይት በቅርቡ እንጀምራለን።ዘራፊና ወንጀለኞች በሕግ መጠየቃቸዉ የግድ ነዉ» ያሉት ይጠቀሳሉ።

 

 

በተጨማሪm አንብ