የጠ/ሚኒስትሩ ማብራሪያና የሕዝብ አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 30.11.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጠ/ሚኒስትሩ ማብራሪያና የሕዝብ አስተያየት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሁለት ዓመታት በመከላከያው፣ በደኅንነት መሥሪያ ቤቱ እና በኢኮኖሚው ዘርፍ አላላውስ ያለ ፈተና ተደቅኖባቸው እንደነበር አመለከቱ። ከትግራይ ክልል ውጪ በሕወሓት የሚመራ ሞትና መፈናቀል ያስከተለ ግጭት በሀገሪቱ መደጋገሙን፤ በዚህ ወቅትም ሀገርን ቀርቶ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉበትን ፈተና ማለፋቸውን አብራርተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:43

«የምክር ቤት አባልት ጥያቄና የጠ/ሚ ማብራሪያ»

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሁለት ዓመታት በመከላከያው፣ በደኅንነት መሥሪያ ቤቱ እና በኢኮኖሚው ዘርፍ አላላውስ ያለ ፈተና ተደቅኖባቸው እንደነበር አመለከቱ። ይህን የገለፁት በጽሕፈት ቤታቸው በተከናወነው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ወቅታዊን የሀገሪቱ ሁኔታ አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ነው። ከትግራይ ክልል ውጪ በሕወሓት የሚመራ ሞትና መፈናቀል ያስከተለ ግጭት በሀገሪቱ መደጋገሙን በማመልከትም በዚህ ወቅት ሀገርን ቀርቶ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉበትን ፈተና ማለፋቸውን አብራርተዋል። የተጠና አደጋ በመከላከያ ሠራዊት ላይ አድርሷል ያሉት የህወሀት ቡድን ወንጀለኞችም ተለቅመው ለፍርድ እንደሚቀርቡ በማመልከትም በዚህ ወቅት ሁሉም ጎረቤት ሃገራት እገዛ ማድረጋቸውንም በመግለጽም አመስግነዋል። የምክር ቤቱ አባላት ሕወሓት በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ ባቀረቡት ጥያቄ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉት ነገር የለም።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው የምክር ቤቱ ልዩ ስብሰባ ከአባላት ለተነሱት ጥያቄዎች የሰጡትን ዘርዘር ያለ ምላሽና ማብራሪያ በርካታ የሀገሪቱ ዜጎች በተለያዩ የመገኛኛ አማራጭ መንገዶች ተከታትለውታል። በማብራሪያዎቹ ላይ የአንዳንዶቹን አስተያየት አሰባስበናል።

ሰሎሞን ሙጬ/ስዩም ጌቱ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች