የጠ/ሚሩ ዉሳኔና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 15.02.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጠ/ሚሩ ዉሳኔና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየት

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በገዛ ፈቃዳቸው ከኢህአዴግ ሊቀመንበርነት እና ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ለመነሳት መጠየቃቸው የተጠበቀ እንደነበር የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ገለፁ። የጠቅላይ ሚንስትሩ ከስልጣን መልቀቅ የሀገሪቱን የፖለቲካ ምህዳር ስለማስፋቱ ግን ጥርጣሬ አላቸው። የፓርቲ አመራሮቹን አነጋግረን ዘገባ አጠናቅረናል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:19

የጠ/ሚሩ ዉሳኔና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየት

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ዛሬ ቀትር ላይ በቴሌቭዝን መስኮት ቀርበዉ የስልጣን መልቀያ ማቅረባቸዉ እንብዛም ያልተጠበቀ እንዳልሆነ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግሥት ስልጣን ይልቀቅ ነዉ የሚለዉ ሲሉ አስተያየታቸዉ የሰጡን የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ባጭሩ ምክትል ሰብሳቢ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፤

በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የመከላከያ ሠራዊትን በተመለከተ ልዩ ፕሮግራሞች እየቀረቡ ስለነበረ አንዳንድ ነገር እንደሚከሰት ይሸት ነበር ሲሉ የገለፁት የቀድሞ የፓርላማ አባል አቶ ልደቱ አያሌዉ ናቸው።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ በበኩላቸዉ ሥራቸዉን በተለያየ ምክንያት መፈፀም ባለመቻላቸዉ መልቀቃቸዉ አስደናቂ አይደለም ነው ያሉት።

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች