የጠቅላይ ሚንስትር ሐይለማርያም መቶ የሥራ ቀናት | እንወያይ | DW | 01.01.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

እንወያይ

የጠቅላይ ሚንስትር ሐይለማርያም መቶ የሥራ ቀናት

በኢትዮጵያ የተደረገዉ የመሪ ለዉጥ፥ ከለዉጡ የተጠበቀዉና የሚጠበቀዉ ፖለቲካዊ እርምጃ፥ የሐያሉ ዓለም በተለይም በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እዉነታ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያደርጉት የዩናስቴትስና የምዕራብ አዉሮጳ መንግሥታት አቋም ብዙ ማነጋገሩ አልቀረም


ጤና ይስጥልኝ እንደምን አመሻችሁ።አቶ ሐይለማይርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ሥልጣን በይፋ ከያዙ ዛሬ ልክ መቶኛ ቀናቸዉ ነዉ።በምዕራቡ ዓለም አንድ መሪ በመቶ የሥልጣን ቀናቱ ያከናወናቸዉን ተግባራት፥ ሊያከናዉን ያቀዳቸዉን እና የቀየሳቸዉን መርሆች መገምገም የተለመደ ፖለቲካዊ ይትበሐል ነዉ።

እንደ ምዕራቡ ዓለም መቶ ቀን መቁጠሩ ለኢትዮጵያ ብዙም አስፈላጊ ባይሆንም በኢትዮጵያ የተደረገዉ የመሪ ለዉጥ፥ ከለዉጡ የተጠበቀዉና የሚጠበቀዉ ፖለቲካዊ እርምጃ፥ የሐያሉ ዓለም በተለይም በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እዉነታ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያደርጉት የዩናስቴትስና የምዕራብ አዉሮጳ መንግሥታት አቋም ብዙ ማነጋገሩ አልቀረም።በዛሬዉ ዉይይታችን ብዙ ከሚያነጋግረዉ ጉዳይ የጎላዉን አንስተን ለመነጋገር የፈለግንበትም ሰበብ ይኸዉ ነዉ።  

ለዉይታችን የአዲሱ የኢትዮጵያ ሥራ፥ የሐገሪቱ ፖለቲካዊ ይዞታና የዉጪዉ ዓለም አቋም የሚል ርዕስ ሰጥተነዋል።አራት እንግዶች አሉን።

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic