የጠቅላይ ሚንስትሩ የክተት ጥሪና የምሑራን አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 23.11.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጠቅላይ ሚንስትሩ የክተት ጥሪና የምሑራን አስተያየት

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲከና ዓለምአቀፍ ግንኙነት መምህር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ግንባር ሄደው ጦሩን ለመምራት መወሰናቸው በጦሩና በደጀኑ ሕዝብ ከፍተኛ ተነሳሽነትን ይፈጥራል ተብሏል። የሕዝብን ተነሳሽነት የሚፈጥር ነው የሚል አስተያየት የሰጡም አሉ። አንድ የደብረማርቆስ ነዋሪም የጠቅላይ ሚስትሩን ውሳኔ ትክክለኛ ነው ብለውታል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:47

በጦሩና በደጀኑ ህዝብ ከፍተኛ ተነሳሽነትን ይፈጥራል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ግንባር ሄደው ጦሩን ለመምራት መወሰናቸው ከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ እንደሚፈጥር አንድ ምሁር አመለከቱ። አንድ የደብረማርቆስ ነዋሪም የጠቅላይ ሚስትሩን ውሳኔ ትክክለኛ ነው ብለውታል። ትናንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ትናንት ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፉት መልዕክት ከዛሬ ጀምሮ ወደ ግንባር በመሄድ ጦርነቱን በበላይነት ይመሩታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን ከተደቀነባት የመከፋፈል አደጋ ለመከላከልና ጦርነቱን ለመቀልበስ ወደ ግንባር ዘምቶ መምራት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ አመራሮችና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግንባር ለመዝመት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ እንዳልሆነ አረጋግጠዋል።

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲከና ዓለምአቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ ቻላቸው ታረቀኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን መወሰናቸው በጦሩና በደጀኑ ህዝብ ከፍተኛ ተነሳሽነትን ይፈጥራል ብለዋል። የደብረማርቆስ ነዋሪው ጋሻዬ ጌታሁንም ውሳኔው የህዝብን ተነሳሽነት የሚፈጥር ነው ብለውታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርበት አመራር መስጠታቸው ውሳኔዎችንም ውሳኔዎችንም ያለመዘግየት እንዲወስኑ እንደሚያግዝ የፖለቲካና ዓለምአቀፍ ግንኙነት መምህሩ አቶ ቻላቸው አስረድተዋል። ውሳኔው የንጉስ ምኒልክን ክተት የሚያስታውስና እንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ እንዲቆም የሚያነሳሳ ተግባር ነውም ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አረአያነታቸውን ለሌሎች አመራሮች በተግባር እያሳዩ ያሉ መሪና ሚናቸውን እየተወጡ

ዓለምነው መኮንን

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

 

 

Audios and videos on the topic