የጠቅላይ ሚንሥትሩ የትግራይ ጉብኝት በነዋሪዎቹ እይታ | ኢትዮጵያ | DW | 11.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጠቅላይ ሚንሥትሩ የትግራይ ጉብኝት በነዋሪዎቹ እይታ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በትግራይ ትናንት ያደረጉት 2ኛ ይፋዊ ጉብኝት በብዙዎች ዘንድ አነጋጋሪ ኾኗል። በትናትናው ዕለት በትግራይ አክሱም ከተማ ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አሕመድ  በቆይታቸው በአደጋ ላይ ያሉትን የአክሱም ሐወልቶች የጎበኙ ሲሆን ከከተማዋ ነዋሪዎችም ጋር ተወያይተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:40

ከነዋሪዎች ጥያቄ ቀርቦላቸው መልስ ሰጥተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በትግራይ ትናንት ያደረጉት ሁለተኛ ይፋዊ ጉብኝት በብዙዎች ዘንድ አነጋጋሪ ኾኗል። በትናትናው ዕለት በትግራይ አክሱም ከተማ ጉብኝት ያደረጉት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አሕመድ  በቆይታቸው በአደጋ ላይ ያሉትን የአክሱም ሐወልቶች የጎበኙ ሲሆን ከከተማዋ ነዋሪዎችም ጋር ተወያይተዋል።  
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከአክሱም ከተማ ህዝብ ተወካዮች ጋር በነበራቸው ውይይት ከሐወልቶቹ ጉዳይ በተጨማሪ ከኤርትራ ጋር ስለተጀመረው ግንኙነትና ሌሎች የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ የሚዳስሱ ጥያቄዎች ቀርቦላቸው ምላሽ ሰጥተዋል። በነዋሪ ተወካዮች ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየታየ ስላለው የሰላምና ድህንነት ሁኔታ ይመለከታል። "በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየታዩ ካሉ ግጭቶችና የፀጥታ መደፍረስ ጋር ተያይዞ በርካታ ዜጎች እየተጎዱ ነው፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሳይቀሩ የግጭት ማእከላት ሆነዋል፣ ተማሪዎች እየተገደሉ ይገኛሉ፣ ይህ መንግስት ለምን አላስቆመውም" ተብሎ ከተሳታፊዎች ለጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ ጥያቄ ቀርቦላቸው እንደነበር የነገሩን  የስብሰባ ተሳታፊ የነበሩ አንድ የአክሱም ከተማ ነዋሪ፡ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ግጭት ሙሉ በሙሉ ማስቆም ባይቻልም ለመቀነስ እየተሰራ ነው ብለው ምላሽ መስጠታቸው ነግረውናል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች የሚያጋጥሙ ችግሮች ለመከላከል የየአካባቢው ማሕበረሰብ ሊሰራ እንደሚገባ መጥቀሳቸውም ተነግሯል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች