የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የፕሬዝዳንት ማክሮ ጋዜጣዊ መግለጫ  | ኢትዮጵያ | DW | 13.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የፕሬዝዳንት ማክሮ ጋዜጣዊ መግለጫ 

ሁለቱ መሪዎች በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፣ ፈረንሳይ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የገጠማቸውን ችግር ለማስወገድ ሙያዊ እና የገንዘብ ድጋፍ የማድረግ ፍላጎት እንዳላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ማክሮ በበኩላቸው ሀገራቸው የኢትዮጵያን ባሕር ኃይል እና የአየር ኃይል በስልጠናም ሆነ በቁሳቁስ እንደምታግዝ ገልጸዋል።  

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:10

የጠ/ሚ ዐብይ እና የፕሬዝዳንት ማክሮ መግለጫ

ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ በቅርስ ጥበቃ፣ በኢንቬስትመንት እና በመከላከያ ዘርፎች ለመተባበር ተስማሙ። ስምምነቶቹም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑዌል ማክሮ በተገኙበት ትናንት ማምሻውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በየሚመለከታቸው የሁለቱ ሃገራት ሚኒስትሮች ተፈርመዋል። ከፊርማው ስነ ስርዓት በኋላ ሁለቱ መሪዎች በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ፣ ፈረንሳይ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የገጠማቸውን ችግር ለማስወገድ ሙያዊ እና የገንዘብ ድጋፍ የማድረግ ፍላጎት እንዳላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ማክሮ በበኩላቸው ጠሚኒስትር ዓብይ ፈረንሳይን በጎበኙት ወቅት በጠየቁት መሠረት ሀገራቸው ፣የኢትዮጵያን ባህር ኃይል እና የአየር ኃይል በስልጠናም ሆነ በቁሳቁስ እንደምታግዝ ገልጸዋል።  ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ አለው።

ዮሐንስ ገብረ እግኢአብሔር
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic