የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም የኬንያ ጉብኝት | አፍሪቃ | DW | 22.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም የኬንያ ጉብኝት

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የኬንያ እና የኢትዮጵያ የንግድ ማህበረሰብ መድረክ ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል ። 35 ተኛው የኢትዮ-ኬንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባም ሁለቱ ሃገራት ከአራት ዓመት በፊት የተፈራረሙት ልዩ የሁለትዮሽ ስምምነት በአፋጣኝ ተግባራዊ በሚሆንበት መንገድ ላይ መክሯል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:36

የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም የኬንያ ጉብኝትየኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በኬንያ የሦስት ቀናት ይፋ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ናይሮቢ ይገባሉ ። አቶ ኃይለማርያም ኬንያ የሚሄዱት የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የንግዱን ማህበረሰብ አባላት አስከትለው ነው ። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የሁለቱን ሃገራት የንግድ ግንኙነት የማጠናከር ዓላማ ባለው የኬንያ እና የኢትዮጵያ የንግድ ማህበረሰብ መድረክ ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል ። ትናንት የተካሄደው 35 ተኛው የኢትዮ-ኬንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባም ሁለቱ ሃገራት ከአራት ዓመት በፊት የተፈራረሙት ልዩ የሁለትዮሽ ስምምነት በአፋጣኝ ተግባራዊ በሚሆንበት መንገድ ላይ መክረዋል ። ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የኬንያ ጉብኝት እና ስለ ኢትዮ-ኬንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ የናይሮቢውን ዘጋቢያችንን ፋሲል ግርማን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬው ነበር ።
ፋሲል ግርማ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic