የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋዜጣዊ መግለጫ | ኢትዮጵያ | DW | 14.04.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋዜጣዊ መግለጫ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ትናንት አዲስ አበባ ላይ በተለያዩ ዓለምአቀፍ፣ አሕጉራዊና ብሄራዊ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ

መለስ ዜናዊ መግለጫ ከሰጡባቸው ውስጣዊ ጉዳዮች አንዱም መጪው የ 2002 ዓ.ም. ምርጫ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርጅታቸው ኢሕአዴግ በጉዳዩ መክሮ ነጻና ግልጽ ምርጫ ለማካሄድ የሚረዳ የውይይት ጽሑፍ ለከፍተኛ የአመራር ዓባላት መበተኑንም አስታውቀዋል። ሰነዱ በነሐሴ ወር መጨረሻ ለሕዝብ ይፋ ይሆናል ነው የተባለው፤