የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት እና የተቃዋሚዎች አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 28.05.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት እና የተቃዋሚዎች አስተያየት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ግንቦት 20ን አስመልክቶ ያስተላለፉት መልዕክት ከዚህ ቀደም ይደመጡ ከነበሩት ለየት ያለ እና የሚደገፍ ነው ሲሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ተናገሩ። የመኢአድ፣ ሰማያዊ እና አረና ትግራይ አመራር አባላት ለዶይቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት መልዕክቱ አንድነትን መተሳሰብን እና መከባበርን የሰበከ ነበር ብለውታል። 

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:31

ተቃዋሚዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልዕክት ደግፈዋል

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የግንቦት 20 መልዕክት በስድስት ጉዳዮች ላይ ያጠነጠነ ነበር። ሁሉም ሰው ወደራሱ ተሰዶ ራሱን በጽሞና እንዲመለከት እና ያሸናፊነት ስነ ልቦና እንዲላበስ ከጎረቤቶቻችን ከቅርብ ወዳጆቻችን ጋር ያሉ ክፍተቶችን በእርቅ መሙላት፣ የታመሙትን በመጠየቅ፣ የታረዙትን በማልበስ እና ደካሞችን በማገዝ መከበር እንዳለበት ጠቁመዋል። የንባብ ባህላችንን በማዳበር፣ የግል እና የአካባቢ ንጽህናን በመጠበቅ እንዲሁም ለሴቶች ክብር በመስጠት ግንቦት 20ን ልናከብረው ይገባልም ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልዕክት እንዴት አገኛችሁት ብለን ከጠየቅናቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች መካከል የመኢአድ ሊቀመንበር ዶ/ር በዛብህ ደምሴ፣ የአረና ትግራይ ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ እንደዚሁም የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ምላሻቸውን ሰጥተውናል። ሶስቱም የፓርቲ መሪዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት ከዚህ ቀደም ከነበረው የተለየ መሆኑን ጠቅሰው ድጋፍ የሚቸረው አይነት እንደሆነ ተናግረዋል። 

ዝርዝር ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።    

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ተስፋለም ወልደየስ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic