የጠቅላይ ሚኒስትሩን የፖለቲካ ለዉጥ የገመገመ ጉባኤ በፓሪስ  | ኢትዮጵያ | DW | 12.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የፖለቲካ ለዉጥ የገመገመ ጉባኤ በፓሪስ 

በኢትዮጵያ የታየዉን ለዉጥ ምክንያት በማድረግ የለዉጡን የአንድ ዓመት ጉዞ የገመገመ ጉባኤ ፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ዉስጥ ተካሂደ።  በጥናቱም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ለዉጥ በአፍሪቃ ቀንድ የጂዮ-ፖለቲካ አዲስ ዉቅር ለዉጥ በቀጠናዉ ያስከተለዉ ስጋትና ተጽእኖ እና የከተሞች መስፋፋት እና የአዲስ አበባ የማንነት ጥያቄ በጥናቱ የተነሱት ጉዳዮች ነበሩ።

 

የኢትዮጵያን ለዉጥ የአንድ ዓመት ጉዞ የገመገመ ጉባኤ ፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ዉስጥ ተካሂደ።  በጥናቱም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ለዉጥ በአፍሪቃ ቀንድ የጂኦ-ፖለቲካ አዲስ ዉቅር በቀጠናዉ ያስከተለዉ ስጋትና ተጽእኖ እና የከተሞች መስፋፋት እና የአዲስ አበባ የማንነት ጥያቄ እንዲሁም የቋንቋ ልዩነት በኢትዮጵያ የሚሉት በጥናቱ ከተነሱት ጉዳዮች ዉስጥ ዋንኞቹ ነበሩ።

ከፓሪስ ዩንቨርስቲ ብሔራዊ ኦርየንታል ቋንቋችና ሥልጣኔዎች ተቋም እንዲሁም ከሌሎች የጥናት ተቋማት የተዉጣጡ የጥናት አቅራቢዎች ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡበት ከፈረንጆቹ የፀደይ ወራት ጋር በማያያዝ የኢትዮጵያ የፀደይ የፖለቲካ ለዉጥ ከአንድ ዓመት በኋላ በሚል ርዕስ ጥናታቸዉን አቅርበዋል። የዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የፖለቲካ ታህድሶ ለዉጥ ከሃገር ዉስጥ አልፎ በቀጠናዉ በሚገኙ ሃገራትም ላይ አወንታዊ ተፅእኖ ማሳረፉን የገለፁት ምሁራኑ፤ በአንፃሩ ብሔርተኝነት የከተሞች መስፋፋትን ተከትሎ የሚነሱ ጥያቄዎች እና ዉጥረቶች፤ የሕዝብ መፈናቀል የጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የአንድ ዓመት ጉዞ ያስተናገዳቸዉ አሉታዊ ክስተቶች መሆናቸዉ በጥናታቸዉ አሳይተዋል። ጉባኤዉን የተከታተለችዉ የፓሪስዋ ወኪላችን ተከታዩን ዘገባ ልካልናለች። 

ሃይማኖት ጥሩነህ 


አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ