የጠቅላይ መለስ ዜናዊ ጋዜጣዊ መግለጫ | ኢትዮጵያ | DW | 16.01.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የጠቅላይ መለስ ዜናዊ ጋዜጣዊ መግለጫ

ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዛሬ የብሄራዊ አንድነት መድረክን ከከፈቱ በኋላ ለዓለም አቀፍ ዜና አውታር ጋዜጠኞች በተመድ የስብሰባ ማዕከል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ።

የጠቅላይ ሚንስትር መለስ

ጠቅላይ ሚንስትር መለስ

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሶማልያ እየወጣ ያለው የኢትዮጵያ ሰራዊት ተልዕኮውን እንዳሳካ ማመናቸውን አስታውቀዋል። በሶማልያ የተፈለገውን ያህል ሰመረጋጋት ባይሰፍንም፡ ሰላም እንዲመጣ ላለፉት ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ ያደረገችውን ጥረት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሳይጠቀምበት በመቅረቱ ተፈጥሮ የነበረውን ዕድል ጥቅም ላይ እንዳልዋለ አስረድተዋል። ከኤርትራ ጋር ስላለው ውጥረት ሁኔታና ዛሬ በአዲስ አበባ ስለተከሰተ ፍንዳታም ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።

ታደሰ እንግዳው