የጎሳ ግጭት በአፋር | ኢትዮጵያ | DW | 10.04.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የጎሳ ግጭት በአፋር

የዓይን ምስክር በግጭቱ ከ10 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል ። የዓይን ምስክሩ እንደሚሉት ግጭቱ አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል ። የግጭቱ መንስኤ የግጦሽ ቦታ ይገባኛል ጥያቄ መሆኑን ተነግሯል ።

በአፋር ክልል በአሚባራ ወረዳ ቦልሃም በተባለ ቦታ በሁለት ጎሳዎች መካከል በተነሳ ግጭት የሰዎች ህይወት አለፈ ። ዘጋቢያችን ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሄር ያነጋገራቸው የዓይን ምስክር በግጭቱ ከ10 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል ። የዓይን ምስክሩ እንደሚሉት ግጭቱ አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል ። የግጭቱ መንስኤ የግጦሽ ቦታ ይገባኛል ጥያቄ መሆኑን ተነግሯል ። በአፋርና በሌሎችም አካባቢዎች የሚነሱ መሰል ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴንና ዘመናዊ ህግን አጣምሮ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ዶቼቬለ ያነጋገራቸው አንድ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ተናግረዋል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic