የጎሳ ወይም የብሔረሰብ ግጭት በኢትዮጵያ | እንወያይ | DW | 20.06.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

እንወያይ

የጎሳ ወይም የብሔረሰብ ግጭት በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ ጎሳ ወይም ብሔር አባላት መካከል በየጊዜዉ የሚከሰቱ ግጭቶች የብዙ ሰዎችን ሕይወት፥ አካልና ንብረት ያጠፋሉ።አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች በሚነሱ ግጭቶች ሰዎች እየተገደሉ፥ እየቆሰሉና እየተፈናቀሉ ነዉ።

አንዳድ ወገኖች የማዕከላዊዉ መንግሥትም ሆነ የአካባባቢያዊ መስተዳድር ባለሥልጣናት ግጭቶቹን ለማስወገድ ብዙም አይጥሩም በማለት ይወቅሳሉ።ሌሎች ደግሞ ባለሥልጣናቱ ራሳቸዉ ግጭቱን ያባብሳሉ በማለት ይከሳሉ።የመንግሥት ባለሥልጣናት በተቃራኒዉ የጎሳ ወይም የብሄር የሚባል ግጭት ባሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ዉስጥ የለም እስከማለት ይደራሳሉ።የትኛዉ ነዉ እዉነት።

የዛሬው ዝግጅት ተወያይቶበታል።

ነጋሽ መሀመድ