የጎርጎሮሳዊዉ ገና በዓል አከባበር | ዓለም | DW | 25.12.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የጎርጎሮሳዊዉ ገና በዓል አከባበር

በረዶዉ ቢጥል ኖሮ የበዓሉ አክባሪዎች «ነጩ ገና ይሉት ነበር።በቅፅሉ።ዘንድሮ ብዙ ቦታ ይሕ አልሆነም።የሰሜኑ ንፍቀ ክበብ ዓየር ነፋስ፥ ዝናብ፥ አንዳዴም ወጀቦ ነዉ ያጠላበት።ድፍርስ ዓየር፥ ጭፍግግ ድባብ።ብሪታንያ ደግሞ ብሶባታል።እንግሊዝ ግን የበዓሉ ወግ አንድም አልቀረበትም።አበሻስ?«ሮም ስትሆን እንደ ሮሞች ሁን» ብሏል ነዉ-ያሉት አዋቂዉ።

ለወትሮዉ በየዓመቱ በዚሕ ሰሞን በሰሜኑ ንፍቀ ክበብ የሚጥለዉ በረዶ ዘንድሮ በአብዛኛዉ ዓለም የለም።የሰሜን አሜሪካ እና የሰሜን አዉሮጳ አየርም ከቀዝቃዛዉ ነጭ በረዶ ይልቅ ነፋስ በቀላቀለ ዝናብ እና ዉሽንፍር እንደ ገረገጣ ነዉ።የእየሱስ ክርስቶስ የልደት ወይም የገና በዓል ግን በመግቢያችን እንዳልኩት የጎርጎሮሳዉያኑን የዘመን ቀመር በሚከተለዉ ዓለም ዘንድ ዘንድሮም-እንደ እስከ ዘንድሮዉ በደማቅ ሥርዓት በየሐገሩ እየተከበረ ነዉ።

ከቤተ-ልሔም እስከ ቫቲካን፥ ከቅዱስ ፔጥሮስ አደባባይ እስከ ዋይት ሐዉስ ቤተ-መንግሥት ተፀልዩዋል።ይበላል፥ ይጠጣል፥ ስጦታዉም እንደየ አቅምና ምርጫዉ ይጎርፋል።ኢራቅ በቦምብ፥ ሶሪያ በመንድፍ፣ መትረየስ፥ ደቡብ ሱዳን በጎሳ ግጭት፥ ማዕከላዊ አፍሪቃ በሐይማኖት ጠብ፥ ሌሎችም ዛሬም በተቀደሰዉ ቀን ደም ይጎርፍባቸዋል።ለአፍሪቃ ቀንድ ስደተኞች፥ ለመላዉ ዓለም ችግረኞችም ዛሬ አይደለም ነገም የበጎ ተስፋ ጭላንጭል አይታይም።ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እኒያን የጦርነት፥ ግጭት፥ የስደት-ድሕነት፥ ጎስቋሎችን እንዘክር-ነበር ያሉት።የሮሙ ወኪላችን ተኽለእግዚ ገብረእየሱስ ተጨማሪ ዘገባ ልኮልናል።


ወደ ፓሪስ እናቅና።ወትሮም ከሰዉነት ሸንቀጥ፥ ሰብሰብ፥ ባለባበስ ሽክ፥ ሸቀርቀር፥ ባአኗኗር ለቀቅ፥ ፈታ፥ በአመጋገብ-አጠጣጥ፥ ረቀቅ፥ ዘነጥ፥ ዘና ማለት የሚወዱት ፈረንሳዮች የገናን አጋጣሚ ቤት-አካባቢያቸዉን ለማስዋብ-ማስጌጥ፥ ከወደ መብል መጠጡ-ጠርቀምቀም አድርገዉ ለመጉረስ-መጎንጨት ነዉ የሚጠቀሙበት።አንዳዶች በተለይ በዕድሜ የገፉ ፈረንሳዮች በዓሉ ነባር ሐይማኖታዊ ይዘቱን አጣ እያሉ መቆጨታቸዉ አልቀረም።የፓሪሷ ወኪላችን ሐይማኖት ጥሩነሕ በተከታዮ ዘገባዎ እንደምትነግረን ግን ያሻዉ፥ ያሻዉን ይበል እንጂ ፈረንሳይ እየተንበሻበሸ ነዉ።

Nahost Weihnachten
በረዶዉ ቢጥል፥ ከመሬት ቢጋገር ኖሮ የበዓሉ አክባሪዎች ነጩ ገና ይሉት ነበር።በቅፅሉ።ዘንድሮ ብዙ ቦታ ይሕ አልሆነም።የሰሜኑ ንፍቀ ክበብ ዓየር ነፋስ፥ ዝናብ፥ አንዳዴም ወጀቦ ነዉ ያጠላበት።ድፍርስ ዓየር፥ ጭፍግግ ድባብ።ብሪታንያ ደግሞ የለንደንዋ ወኪላችን ሐና ደምሴ እንደታዘበችዉ ብሶባታል።እንግሊዝ ግን የበዓሉ ወግ አንድም አልቀረበትም።አበሻስ-«ሮም ስትሆን እንደ ሮሞች ሁን» ብሏል ነዉ-ያሉት አዋቂዉ።


በአሜሪካኖች እናሳረግ።በብዙ ነገር የሁሉም ዓለም አንደኞች ናቸዉ።በገና በዓልስ? አላወዳደርናቸዉም። ይልቅዬ አሜሪካዊዉ-ኢትዮጵያዊዉ የአሜሪካኖቹን በዓል ማክበር አለማክበሩን ነዉ-የምንቃኘዉ።ቅይጥ ሕዝብ፥ ድብልቅ በዓል።የዋሽግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዘገባ አለዉ።

ወኪሎች

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ
Audios and videos on the topic