የጎርጎሮሳዊዉ ቀመር የገና በዓል | ዓለም | DW | 25.12.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የጎርጎሮሳዊዉ ቀመር የገና በዓል

በጎርጎሮሳዊ የዘመን ቀመር 2012ዓ,ም የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በመላዉ ዓለም በሚገኙ ይህን አቆጣጠር በሚከተሉ ክስቲያኖች ዘንድ ተከበረ። የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16 ተኛ በግጭት በሚታመሱት በእስራኤልና ፍልስጤም በሊባኖስ በሶሪያ በኢራቅንና በአጎራባች ሃገሮች የሠላም ጥሬ አስተላለፉ ።

በርካታ ተከታዮች ባሏት የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን መንበር ሮም የገና በዓልን እንደከዚህ በፊቱ እና እንደተለመደዉ የማክበሩ ሁኔታ መለወጡ ተሰምቷል። ይህንም ሆኖ ግን ዛሬም በዓሉ በእምነቱ ተከታዮች እና አባቶች ደምቆ በጴጥሮስ ወጳዉሎስ መንበር ቫቲካን ሥርዓቱ ሳይጓደል ምሽቱን ተከብሯል፤ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኑዲክት 16ኛም በየዓመቱ እንደሚያደርጉት በተለያዩ ቋንቋዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Weihnachten in Bethlehem

ቤተልሔም

አሜሪካዉያን ለወትሮዉ ገናን ደመቅ አድርገዉ ማክበሩን ያዘወትሩ እንዳልነበር ዘንድሮ የዋጋ ንረቱና በቅርቡ በኒዉታዉን ከተማ ከ20 በላይ ህፃናት የተገደሉበት አጋጣሚ በዓላቸዉን ያቀዘቀዘዉ መስሏል። በእስራኤል ደግሞ በቤተልሄም፤ በናዝሬት፤ በሃይፋ ሃዳርና በገሊላ አካባቢዎች የእምነቱ ተከታይ የሆነዉ የሀገሬዉ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች በዚህ ወቅት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተወለደባት በሚታመንባት ምድር በመገኘት በዓሉን አክብረዋል። በቤተልሄሙ ስነ ስርዓት ላይ በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያን ፍልስጤሞችና በአሉን ለማክበር ከመላው አለም የተሰባሰቡ ምዕመናን ተገኝተዋል ።

Chapel of Silent Night in the community of Oberndorf. At this place the St. Nicola church had its place, in this church the Silent Night, Holy Night song, the World′s most popular Christmas Carol, was composed and first sung.

ኦስትሪያ ኦበንዶርፍ የሰላም ሌሊት ቤተፀሎት

በዚህ በጀርመንና በበርከታ የአዉሮጳ ሀገራት ብትን የሚለዉ በረዶ ሳይወርድ ቅዝቃዜዉም ሳይጠና ግን በዝናብ ማለዳዉ ጀምሮ ረፈድ ሲል ጸሃይ ፍንትዉ ብላ ወጥታለች። ምንም እንኳ ነጩን ገና ማየት ባይችሉም የገና በዓል ግን የወትሮ ወጉን አላጣም፤ ትናንት ከቀትር በኋላ አንስቶ እረጭ ያለዉ አዉድ በዓሉ በርግጥም የሰላምና የደስታ ሌሊት መሆኑን እንደዜማዉ አመላክቷል። ከሮማ ቫቲካን፤ ከእስራኤል ናዝሬት፤ ራዲዮ ጣቢያችን ከሚገኝበት ቦን ጀርመን እንዲሁም ከዋሽንግተን ዲሲ የተጠናቀሩ ዘገባዎችን ያድምጡ።

ተኽለእግዚ ገብረኢየሱስ

ግርማዉ አሻግሬ

ገመቹ በቀለ

አበበ ፈለቀ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic