የጎርደን ብራውን ፈተና | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 09.06.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የጎርደን ብራውን ፈተና

በብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጎርደን ብራውን የሚመራው የሌበር ፓርቲ ሰሞኑን በታሪኩ ታይቶ የማይታወቅ ሽንፈት ተደራርቦበታል ።

default

...የጀመርኩትን ሳልጨርስ ?ሙጥኝ...

ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የአካባቢና የማዘጋጃ ቤቶች ምርጫ ጥቂት ድምፅ ያገኘው ሌበር ባለፈው ሳምንት መጨረሻው የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ ደግሞ ታይቶ የማይታወቅ ክስረት ነው የደረሰበት ። የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጎርደን ብራውን በገንዘብ ሚኒስትርነታቸው ዘመን የተደነቁ ቢሆንም የዛሬ ሁለት ዓመት ስልጣን ከተረከቡ ወዲህ ግን የአመራር ችሎታቸው ጥያቄ ውስጥ ወድቋል ። የሌበር ፓርቲ አባላት ብራውን ከስልጣን እንዲወርዱ መጠየቅ ከጀመሩ ሳምንታት ተቆጥረዋል ። የለንደኑ ዘጋቢያችን ድልነሳ ጌታነህ ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ድልነሳ ጌታነህ / ሂሩት መለስ /ሸዋዬ ለገሠ