የግጥም ፍቅር - ካሳውማር ዉበት | ባህል | DW | 30.10.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የግጥም ፍቅር - ካሳውማር ዉበት

በእስራኤል ሲኖሩ ወደ ሠላሳ ሁለት ዓመታት እንደሆናቸዉ የሚናገሩት አቶ ካሳዉማር ዉበት የዛሬዉ እንግዳችን ናቸዉ ካሳዉማር፤ ኢትዮጵያ ሳሉ ተደራራቢ የወጣት ሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ ለጥቆም ተደራራቢ የገበሪዎች ሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ ሆነዉ በኖሩበት የገጠር ገበሪ ማኅበር ማገልገላቸዉን ይናገራሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 12:13
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
12:13 ደቂቃ

ሥነ-ግጥምን በፍቅር «ካሳማሩ ዉበት»

የመሠረተ ትምህትም ፤ ተምረዋል አስተምረዋልም። እሳቸዉ ፊደል ቆጥረዉ በራሳቸዉ ጥረት ተምረዉ ዛሬ ኮንፒዉተሩን ይዘዉ ግጥሞቻቸዉን ይቋጥሩ እንጂ እስከዚህ ክፍል ድረስ ተማርኩ የሚሉት የለም እንደዉ ግን በአስካላዉ ትምርት አምስተኛ ስድስተኛ ክፍልን እንዳጠናቀቁ ፤ ያስባሉ፤ ይገምታሉም። እስራኤልም የይብራይስጡን ቋንቋ በሙሴ ዘመቻ ከካርቱም ተነስተዉ እስራኤል ከገቡ በኋላ  ትንሽ ተምረዉ ነዉ ያቋረጡት፤ ታድያ የይብራይስጡን ፊደልም ቢሆን በኢትዮጵያ ልጅ ሳሉ ለከብት ጥበቃ ከመላካቸዉ በፊት በነበሩበት ትምህር ቤት ነዉ የቆጠሩት።

አቶ ካሳዉማር ያለ ሥነ- ግጥም መኖር አይችሉም፤ በእስራኤል በተለይ በሥነ- ግጥማቸዉ በሥነ-ጥሑፋቸዉ ነዉ የሚታወቁት። ካሳ ማር የቋጠርዋቸዉን ሥነ-ግጥሞች አሰባስበዉ አሰትመዉ ለአንባብያን ለማቅረብ የመድብሉን ምረቃ ቀን ቀጠሮም ይዘዋል።  አቶ ካሳዉማር መጨረሻ የቋጠርዋት ሥነ-ግጥም ስለ አዲሱ የስልክ ቴክኖሎጂ «ዋትስአፕ» እንደሆን ይናገራሉ። የግጥም ደራሲዉን አቶ ካሳዉማር ዉበትን በዶይቼ ቬለ ስም በማመስገን ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic