የግጥም መድብል - እዉነትም እኛ ..... | ባህል | DW | 25.11.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የግጥም መድብል - እዉነትም እኛ .....

የታዋቂዉ ጋዜጠኛ እና ደራሲ አበራ ለማ ናጋቲ ካ ያ ጓሼ ኮ ከሚለዉ ለሎሪት ጸጋዮዪ ገብረመድህን ማስታወሻነት ከጻፉት የተወሰደን ግጥም ነዉ በመፕሮግራሙ መጀመርያ የምታደምጡት የጋዜጠኛና የደራሲ አበራ ለማ ሃያ አምስት ምርጥ ስነ-ግጥሞች ስብስብ በዲቪዲ በከለር ድምጽ ቅንብር ለታዳሚዎች እይታና ጆሮ ቀርበዋል።

default

እነዚህ በዲቪዲ በምስል እና ድምጽ ቅንብር የቀረቡት ስራዎች የምረቃ ስነ-ስርአት በልዩ ልዩ የአዉሮጻ እና አዉሮጻ ከተሞች በመካሄድ ላይ ነዉ። በለቱ ዝግጅት ደራሲ አበራ ለማን ስለ አቀረቡት የግጥም ስራቸዉ ስለ ጋዜጠኝነት ተመክሮአቸዉ ጠይቀን ልናካፍል ይዘናል ለጥንቅሩ አዜብ ታደሰ ነኝ መልካም ቆይታ

ታዋቂዉ ደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ አስር ያህል አጫጭር የልብ ወለድ ስራዎች የግጥም መድብሎች እንዲሁም እንዲሁም የስነ-ጥበብ እና የጋዜጠኝነት ማጎልበቻ መጻህፍትን ለህትመት አብቅተዋል። በቅርቡ ደግሞ በአይነቱ ምናልባትም የመጀመርያ የተባለለትን በምስል የታጀበ የግጥም ስራዎቻቸዉን በዲቪዲ ለታዳምያን አቅርበዉ በአዉሮጻ የተለያዩ አገራት የምረቃ እና የግምገማ ፕሮግራሙ ቀጥሎአል እስካሁን ይህ በዲቪዲ የተካተተዉ የግጥም መድብል ከአምስተርዳም ተነስቶ ቤልጂየም ሉቨን ላይ ፣ ዴንሃግ እንዲሁም ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ኦስሎ ላይ የምረቃዉ ስነ-ስርአት ተካሄድዋል። ደራሲዉ በአዉሮጻ ዉስጥ ያላቸዉን ፕሮግራም ካጠናቀቁ በኳላ ለምረቃዉ ስነ-ስርአት ጉዞአቸዉን ወደ ተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች እንደሚያደርጉ ይህንን ዲቪዲ የካሜራና ምስል ቅንብር ያደረገዉ ጋዜጠኛ ክብረት መኮንን ይገልጻል። ጋዜጠኛ እና ደራሲ አበራ ለማ በኢትዮጽያ ቀደም ሲል በኢትዪጽያ ራድዮ በራድዮ ጋዜጠኝነት ከዝያም ቆየት ብሎ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በተለይ በባህል ዙርያ የጋዤጠኝነት ሞያ አገልግለዋል። ዝግጅቱን ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ