የግዕዝ ትንሣኤ | ባህል | DW | 17.05.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የግዕዝ ትንሣኤ

ግዕዝ ማንቀላፋቱ እንጂ ግብዐተ-መሬቱ ተፈፀመ መባሉ ተቀባይነት የለውም። ይልቁንስ የግዕዝ ትንሣኤው እየተፋጠነ ህፃናት ሳይቀሩ በልሳነ-ግዕዝ መነጋገር ጀምረዋል። «የልሳነ-ግዕዝ ወዳጆች ማህበር» መስራች ከሆኑት ከመምህር ደሴ ቀለብ ጋር ተወያይተናል፤ አብራችሁን ቆዩ።

default

በኢትዮጵያ ግዕዝም ይፈልቃል

«የልሳነ-ግዕዝ ወዳጆች ማህበር» በሚል ስያሜ የግዕዝ ቋንቋን ትንሣኤ ለማፋጠን የሚንቀሳቀሰው ማህበር በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በርካታ ሰዎችን ያካተተ ታላቅ ጉባኤ ማካሄዶ ታውቋል። ማህበሩ ባደረገው ውይይትም በስሩ የግዕዝ ተናጋሪ ቤተሰብን ማቋቋሙም ተገልጿል። ይህ ማህበር በትንሹ ከሁለት ሺህ በላይ አባላት ቢኖሩትም፤ ያለምንም መዋጮና ገቢ ግን ለግዕዝ ቋንቋ እድገት በሚቆረቆሩ ግለሰቦች ቋንቋውን ለማስፋፋት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን መምህር ደሴ አብራርተዋል። ለመሆኑ የግዕዝ ተናጋሪ ቤተሰብ የሚያካትተው እነማንን ነው?

ማንተጋፍቶት ስለሺ