የግዕዝ ትንሣኤ- ክፍል ሁለት | ባህል | DW | 23.05.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የግዕዝ ትንሣኤ- ክፍል ሁለት

በዚህ አጋጣሚ የግዕዝ ቋንቋን ለመማር መረጃዎችን ለማግኘት ለምትፈልጉ ሁሉ በልሳነ-ግዕዝ የኢሜል አድራሻ geezaau@yahoo.co.uk ብላችሁ ብትፅፉ አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት እንደምትችሉም እንገልፃለን።

በኢትዮጵያ ግዕዝም ይፈልቃል

በኢትዮጵያ ግዕዝም ይፈልቃል

ባለፈው ሣምንት፤ ለግዕዝ ቋንቋ ትንሳኤ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ከሚገኙ አንድ የዩኒቨርሲቲ ምሁር ጋር ቆይታ ማድረጋችን ይታወቃል። ምሁሩ መምህር ደሴ ቀለብ ሲሰኙ፤ የልሳነ-ግዕዝ ወዳጆች ማህበር አባልና ከመስራቾቹም አንዱ ናቸው። ዛሬ ባለፈው ሣምንት ካቆምንበት በመቀጠል ከምሁሩ ጋር ያደረግነውን ቀሪ ቆይታ እናቀርባለን። የዛሬው ዝግጅታችን በአዲስ አበባ ከተማ ተወልዶ ያደገ አንድ ወጣትንም አካቷል። ወጣቱ የግዕዝ ቋንቋን ከአባቱ ተምሮ በሚገባ እያቀላጠፈው እንደሚገኝ ገልጾልናል።

ከጥንትም አንስቶ የግዕዝ ቋንቋ ከአማርኛው ቋንቋ ጋር የመወራረሱን ያህል በተለምዶ ስህተት አድርገናቸው የቆዩ ቃላት እንዳሉም መምህር ደሴ ቀለብ ገልፀዋል። ለአብነት ያህልም፥ እንግሊዘኛው Mass media የሚለውን አማርኛው የግዕዝን እርዳታ በመማፀን ሲያስቀር በተሳሳተ መልኩ እንደሆነ ያብራራሉ። በሬዲዮ ሙዚቃን በመተንተንና ግዕዝን በማስተማር ተግባር ላይ የተጠመደው ወጣት ሰርፀ ፍሬ-ሠንበት በበኩሉ አማርኛ ቋንቋ ከግዕዝ ከሃምሳ በመቶ በላይ ቃላትን እንደተዋሰ ገልጿል።

ይህን የኢትዮጵያውያን ሀብት የሆነውን የግዕዝ ቋንቋ ካንቀላፋበት በማስነሳት ትንሣኤውን ለማፋጠን ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ባሻገር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀላፊነት እንዳለበት ለማመላከት እንወዳለን። በነገራችን ላይ የግዕዝ ቋንቋ በልሳነ-ግዕዝ ማህበር ስር በሚገኘው የግዕዝ ተናጋሪ ቤተሰብ ዘንድ አፍ መፍቻ መሆኑ እንደተበሰረም ታውቋል። በዚህ አጋጣሚ የግዕዝ ቋንቋን ለመማር መረጃዎችን ለማግኘት ለምትፈልጉ ሁሉ በልሳነ-ግዕዝ የኢሜል አድራሻ geezaau@yahoo.co.uk ብላችሁ ብትፅፉ አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት እንደምትችሉም እንገልፃለን። በግዕዝ ቋንቋ ትንሣኤ ዙሪያ ያደረግነው ዝግጅት በዚህ ይጠናቀቃል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ