የግዕዝ ቋንቋ ጥናት በጀርመን | ባህል | DW | 10.10.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የግዕዝ ቋንቋ ጥናት በጀርመን

በአክሱም መንግሥት መደበኛ ቋንቋ እንደነበር ይነገራል፤ የግዕዝ ቋንቋ። ዛሬም ድረስ የግዕዝ ቋንቋ በኢትዮጵያ፤ በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እንዲሁም በኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጥቅም ላይ ይዉላል።

የሴማዊ ቋንቋዎች አባል የሆነዉ የግዕዝ ቋንቋ፤ የጥንት የሰዉ ልጅ ታሪክን ያካትታል ሲሉ ምዕራባዉያን በግዕዝ ቋንቋ የተፃፉ ጥንታዊ መጻህፍትን በማገላበጥ ማጥናት ከጀመሩ ዘመናትን አሳልፈዋል። የኢትዮጵያ ባህል ቋንቋ ጥናት በአዉሮጳ እንዲጀመር ያደረገች የመጀመርያዋ አዉሮጳዊት ሀገር ጀርመን መሆንዋ ይታወቃል። ጀርመናዉያን በአፍሪካ ቀንድ በኢትዮጵያና በኤርትራ ከጥንት ጀምሮ ሲያገለግል ስለቆየዉ ስለ ግዕዝ ቋንቋ ማጥናት ከጀመሩ እጅግ ብዙ ዓመታትን አስቆጥረዋል። በርሊን በሚገኘዉ የዓርብኛ እና ሴማዊ «ሴሜቲክ» ቋንቋ ተቋም ከጀርመናዉያኑ ጋር ጥናት ሲያደርጉ የቆዩት ዶክተር ሙሉቀን አንዱዓለም፤ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ጀርመን ከመምጣታቸዉ በፊት በኢትዮጵያ በትልልቅ በዓላት ላይ ፓትርያርኩ በባሉበት ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ሆነዉ ቅኔ በመቀኘታቸዉ እንደሚታወቁ ነግረዉናል፤በተወለዱበት በጎጃም አካባቢ በህጻንነታቸዉ ፊደል ቆጥረዉ ወንጌል አንብበዉ ዳዊት ደግመዉ ፤ ፆመ ድጓ ተምረዉ፤ ቅኔ ቤትም ሄደዉ ከጨጨረሱ በኋላ፤ ለማስትሪት ማዕረግ እስኪደርሱ የዘመናዊዉን ትምህርት ሀገር ቤት ነዉ ያጠናቀቁት። በኢትዮጵያ የግዕዝ ቋንቋ እየሰፋ መሆኑን ባደረጉት ጥናት ማየታቸዉን የገለፁልን ዶክተር ሙሉቀን አንዱዓለም የለቱ እንግዳችን ናቸዉ ሙሉ ቅንብሩን ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ሸዋዪ ለገሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች