የግንቦት ሰባት ተከሳሾች ጉዳይ | ኢትዮጵያ | DW | 08.12.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የግንቦት ሰባት ተከሳሾች ጉዳይ

የኢትዮጵያን መንግሥት በሐይል ለመገልበጥ ተንቀሳቅሰዋል የሚል ክስ የተመሰረተባቸዉን የጦር መኮንኖች እና የግንቦት ሰባት አባላትን ጉዳይ ዛሬ የተመለከተው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ፣ አቃቤ ህግ እንዲወረስለት የጠየቀው የተከሳሾች ንብረት በዝርዝር ተለይቶ እንዲቀርብለት ጠይቋል ።

default

አቃቤ ህግ በበኩሉ በተከሳሽ ቤተሰቦች የቀረበው የንብረት ይለይልን ጥያቄ በጣልቃ ገብቶ ሊታይ አይችልም ጥያቄው ከችሎቱ ውሳኔ በኃላ የሚታይ ነው ሲል ተከራክሯል ። በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ አቃቤ ሕግ እንዲወረስ የጠየቀውን ንብረት በዝርዝር ለይቶ እንዲያቀርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ።

ታደሰ ዕንግዳው

ሂሩት መለሰ/አርያም ተክሌ