የግብፅ ፕሬዝዳት ዉሳኔና ተቃዉሞዉ | አፍሪቃ | DW | 28.11.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የግብፅ ፕሬዝዳት ዉሳኔና ተቃዉሞዉ

የአደባባይ ሠልፍ፥ተቃዉሞዉ እየጠነከረ ሔደ።ትናንት አደባባይ የወጣዉ ተቃዋሚ ወደ ሰወስት መቶ ሺሕ ተገምቷል። ተቃዋሚዎችን የሚቃወሙት ወይም ፕሬዝዳንቱን የሚደግፉት ወገኖችም አደባባይ አይዉጡ እጅ ቁጣ ንዴታቸዉ እያየለ መሆኑን አልሸሸጉም።እና በሳቸዉ ቋንቋ ግብፅ ለሁለት ተገመሰች

A general view of anti-Mursi protesters gathering at Tahrir Square in Cairo November 27, 2012. Opponents of President Mohamed Mursi clashed with Egyptian police on Tuesday as thousands of protesters stepped up pressure on the Islamist to scrap a decree they say threatens the nation with a new era of autocracy. REUTERS/Mohamed Abd El Ghany (EGYPT - Tags: CIVIL UNREST POLITICS TPX IMAGES OF THE DAY)

ተሕሪር አደባባይ-ሐሙስ

የግብፁ ፕሬዝዳንት መሐመድ ሙርሲ በቅርቡ የሐገሪቱን ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ሥልጣን የሚገድብ ደንብ መደንገጋቸዉ ያስቆጠዉ ሕዝብ በየአደባባዩ የሚያደርገዉ ተቃዉሞ እንቀጠለ ነዉ።ፕሬዝዳት ሙርሲ ትናንት ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ጋር ቢነጋገሩም ያወጁትን ደንብ እንደማይሽሩት አስታዉቀዋል።ሙርሲ በአቋማቸዉ መፅናታቸዉ ከተነገረ በሕዋላ ፕሬዝዳንቱንና የፕሬዝዳንቱን ፓርቲ የሚቃወሙ ወገኖች በየከተማዉ የሚያደርጉት የተቃዉሞ ሠልፍ ተጠናክራል።ዘገቦች እንደጠቆሙት ትናንት ካይሮ ዉስጥ በተደረገዉ የተቃዉሞ ሠልፍ የተሳተፈዉ ሕዝብ ቁጥር የቀድሞዉ ፕሬዝዳት ሆስኒ ሙባረክ ከሥልጣን ከተወገዱ ወዲሕ እጅግ ከፍተኛዉ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።


ያ-የነፃነት አብነቱ፥ የመስዋዕትነት ተምሳሌዉ፥ የሕዝባዊ አብዮት መናኸሪያዉ አደባባይ ሰሞኑንንም እንዳምና ሐቻምናዉ በተቃዉሞ ሠልፈኛ ተጨናንቋቋል።ተሕሪር።ያሁኑ ሠልፍ-ተቃዉሞ ያነጣጠረዉ ሕዝባዊዉ አብዮት በወለደዉ ሕዝባዊ ምርጫ ለሥልጣን በበቁት ፕሬዝዳት ላይ ነዉ።መሐመድ ሙርሲ።


ተንታኞች እንደሚሉት የግብፅ ሕዝባዊ አብዮት ታላቅ ድል በከፊል የመከሽፉ ምልክት።በግብፅ የዘመናት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሕዝብ ድምፅ የተመረጡት መሐመድ ሙርሲ ተቃዋሚዎቻቸዉ እንደሚሉት አንድም የዘመኑ ፈርዖን አለያም ዳግማዊ ሆስኒ ሙባረክ ናቸዉ።ወይም ለመሆን ይሞክራሉ።

FILE - In this Friday, July 13, 2012 file photo, Egyptian President Mohammed Morsi speaks to reporters during a joint news conference with Tunisian President Moncef Marzouki, unseen, at the Presidential palace in Cairo, Egypt. Egypt’s Islamist president may hail from the fiercely anti-Israeli Muslim Brotherhood, but in his first major crisis over Israel, he is behaving much like his predecessor, Hosni Mubarak:. He recalled the ambassador and engaged in empty rhetoric supporting Palestinians. Mohammed Morsi is under pressure at home to do more but he is just as wary as Mubarak about straining ties with the United States. (Foto:Maya Alleruzzo, File/AP/dapd)

ፕሬዝዳንት ሙርሲየሙርሲን ተቃዋሚዎች ላደባባይ ሠልፍ ያሳደመዉ፥ ሙርሲንና የቀድሞ ፓርቲያቸዉን ሙስሊም ወንድማማቾችን የሚያስወግዝ፥ የሚያስረግመዉ ፕሬዝዳንቱ የሐገሪቱን ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ሥልጣን የሚገድብ ደንብ ማወጃቸዉ ነዉ።በአዋጁ መሠረት ሕገ-መንግሥታዊዉ ፍርድ ቤት የሐገሪቱን ምክር ቤትና ሕገ-መንግሥታዊ ሸንጎን የማገድ ወይም የመበተን ሥልጣኑ ተገፏል።

እርምጃዉ የቀድሞዉ አምባገነን መሪ ሆስኒ ሙባረክ ለሾሟቸዉ ለሕገ-መንግሥታዊና ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች የሞት ሽረት ጥያቄ ነዉ።የሙርሲ ተቃዉሚ ፖለቲከኞችና አደባባይ ያስወጡት ሕዝብ ደግሞ ግብፅን «በሸሪዓ ሕግ ለመግዛት» ይፈልጋል የሚሉት የሙስሊም ወንድማማቾች ሐገሪቱን እንዳሻዉ ለመግዛት ፕሬዝዳንቱ ጥሩ መደላድል መፍጠራቸዉ ነዉ።

«የሙስሊም ወንድማማቾች ላዕላይ መሪ እዉነተኛዉ የግብፅ ገዢ ነዉ።ግቦፆችና ሙርሲ የሚያደርጉትን የሙስሊም ወንድማማቾች እንዲያደርጉ የሚነግሯቸዉን ነዉ።»

አሉ የካይሮዋ ነዋሪ።

የፕሬዝዳንቱ ደጋፊዎች ተቃዋሚዎቻቸዉን ለመቃወም አደባባይ ለመዉጣት ተዘጋጅተዉ ነበር። ፕሬዝዳንቱ ግን አይሆንም አሉ።ፕሬዝዳንቱ ፖለቲካዊ መልክና ባሕሪ የተላበሰዉን ቁጣና ተቃዉሞ ለማቀዝቀዝ ትናንት ከዳኞቹ ጋር ተነጋግረዉ ነበር።አልተስማሙም።

ዉይይቱ ያለ ዉጤት ማብቃቱ እንደተሰማ የአደባባይ ሠልፍ፥ተቃዉሞዉ እየጠነከረ ሔደ።ትናንት አደባባይ የወጣዉ ተቃዋሚ ወደ ሰወስት መቶ ሺሕ ተገምቷል። ተቃዋሚዎችን የሚቃወሙት ወይም ፕሬዝዳንቱን የሚደግፉት ወገኖችም አደባባይ አይዉጡ እጅ ቁጣ ንዴታቸዉ እያየለ መሆኑን አልሸሸጉም።እና በሳቸዉ ቋንቋ ግብፅ ለሁለት ተገመሰች።

Protesters gather at Tahrir square in Cairo November 23, 2012. Angry youths hurled rocks at security forces and burned a police truck as thousands gathered in central Cairo to protest at Egyptian President Mohamed Mursi's decision to grab sweeping new powers. Police fired tear gas near Tahrir Square, heart of the 2011 uprising that toppled Hosni Mubarak at the height of the Arab Spring. Thousands demanded that Mursi should quit and accused him of launching a coup. REUTERS/Mohamed Abd El Ghany (EGYPT - Tags: POLITICS CIVIL UNREST)

ተሕሪር አደባባይ-ቅዳሜ

«ገሚሱ ከሙርሲ ጎን ቆሟል። የተቀሩት ገሚሶቹ እሳቸዉን ይቃወማሉ።እንግዲሕ ማን እንደሚያሸንፍ እናያለን።ፍትሕ ያሸንፋል።»

በፊት እንደታሰበዉ ቢሆን ኖሮ ዛሬ አዲሱ ሕገ-መንግሥት ተረርቅቆ የሚያበቃበት ዕለት በሆነ ነበር።አልሆነም።የዉዝግብ፥ ንትርክ ቀን እንጂ። ዉዝግቡ ባስከተለዉ ግጭት እስካሁን ሰወስት ሰዎች ተገድለዋል።ዉዝግቡም እንደቀጠለ ነዉ።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች