የግብፅ ወቅታዊ ሁኔታና ዓለም አቀፍ አስተያየት፣ | አፍሪቃ | DW | 15.08.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የግብፅ ወቅታዊ ሁኔታና ዓለም አቀፍ አስተያየት፣

ግብጽ ውስጥ ትናንት የተወሰደውን የኃይል እርምጃ፤ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በጥብቅ ነው ያወገዘው።

በግብፅ ፣ የሽግግሩ መስተዳድር ፀጥታ አስከባሪ ኃይሎች ፣ ከሥልጣን የተወገዱት ፕሬዚዳንት ሙሐመድ ሙርሲ ደጋፊዎች ፣ ካይሮ ውስጥ በከተማይቱ አንዳንድ አደባባዮች ከመሸጉባቸው ጣቢያዎች እንዲለቁ ለማስገደድ በወሰዱት እርምጃ የብዙ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱ እንደታወቀ፤ የአፍሪቃ ኅብረት የሰላምና ፀጥታ ኮሚሽን፤ ያቋቋመውን አጥኚ ቡድን ፤ በአፋጣኝ ልኳል። የግብፅን ወቅታዊ ይዞታ በተመለከተ፣ በዚያው በአፍሪቃ ኅብረት ምክክር መደረጉም ታውቋል።

ትናንት ፣ የግብፅ ፖሊስና ወታደር 12 ሰዓት ያህል በወሰደው የኃይል እርምጃ እንደ ሙስሊም ወንድማማች ማኅበር መግለጫ ከሆነ ከ 2,000 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በሺ የሚቆጠሩ ደግሞ ቆስለዋል።የሽግግሩ መንግሥት በበኩሉ፤ 43 ፖሊሶች እንደተገደሉበት ያስታወቀ ሲሆን፤ ገለልተኛ የዜና አውታሮች፣ ቢያንስ ከ 250 በላይ ተገድለዋል ይላሉ። ባሁኑ ወቅትም፣ በካይሮና በሌሎች 11 ከተሞች፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የወጣ ሲሆን የሰዓት እላፊ ገደብም ተጥሏል። ከአካባቢው የሚገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ሁኔታው አስፈሪና አሳሳቢ ነው።


ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ/ገበያው ንጉሤ

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic