የግብፅ ኮፕቶች 118ኛዉ የሃይማኖት አባት | አፍሪቃ | DW | 05.11.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የግብፅ ኮፕቶች 118ኛዉ የሃይማኖት አባት

የግብፅ ኮፕት ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች 118ኛ ሃይማኖት አባት ትናንት በይፋ ተመርጠዋል። ቤተክርስቲያኒቱን ለ42ዓመታት በማስተዋል እንዳስተዳደሩ የሚነገርላቸዉ ፓትሪያርክ አቡነ ሺኖዳን የሚተኩት አባት አቡነ ቴዎድሮስ የተመረጡት የግብፅ ኮፕት፤

ቤተክርስቲያን በምትከተለዉ በእጩነት ከቀረቡ ሶስት አባቶችን አንዱን በእጣ የመለየት ስልት ነዉ። ስነስርዓቱን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የወከሉ አባቶችን ጨምሮ በአካል ከሁለት ሺህ በላይ ታዛቢዎች ተከታትለዋል። ምርጫዉ እንዳይጭበረበርና የሰዎች ጣልቃ ገብነት እንዳይኖርበት በጥንቃቄ መከናወኑን የፈረንሳይ የዜና ወኪል ከካይሮ ዘግቧል። ከህዝቡ 10 በመቶ መሆናቸዉ የሚገለፀዉ የግብፅ ኮፕት ክርስቲያኖች ለአክራሪ ሙስሊሞች ተፅዕኖና ጥቃት መጋለጣቸዉን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ከዚህ አንፃር የተመረጡት አባት ምን ይጠብቃቸዋል፤ ሂደቱን ከቅርብ ርቀት የተከታተለዉን የጂዳዉ ወኪላችንን ስለሁኔታዉ በስልክ ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ አነጋግሬዋለሁ፤

ነብዩ ሲራክ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic