የግብፅ ብጥብጥና የአውሮፓ ኅብረት | ዓለም | DW | 10.07.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የግብፅ ብጥብጥና የአውሮፓ ኅብረት

በግብፅ በተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና በህዝቡ መካከል ልዩነቱ መስፋቱና ፍጥጫውም ማየሉ የግብፅን የፖለቲካ ሂደት ይብሱን እንዳያሰናክለው ሃገሪቱንም ወደ ፖለቲካ ትርምስ እንዳይከታት የሚያሰጋ ነው ሲል የአውሮፓ ህብረት አሳሰበ።

የህብረቱ ባለሥልጣናት የግብፅ አደገኛ አዝማሚያ ወደ ሌሎች የአካባቢ ሃገራት እንዳይዛመት የሚያሰጋ እንደሆነ ጠቁመዋል። ከብራሰልስ ይህ ሲሰማ ካይሮ ደግሞ በኃይል የተወገዱት የግብጹ ፕሬዝዳንት የመሐመድ ሙርሲ ደጋፊዎች ዛሬም ሙርሲ ወደ ቀድሞው ቦታቸው እንዲመለሱ መጠየቃቸውን ቀጥለዋል። የግብፅ አቃቤ ህግ ደግሞ ህዝብን ለአመፅ አነሳስተዋል ያላቸው የሙስሊም ወንድማማቾች ማህበር አባላት መሪዎች እንዲታሰሩ  ትዕዛዝ አስተላልፏል። በግብፅ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንትነት የተሰየሙት አድላዊ ማንሱር የሽግግሩን ሂደት መጀመራቸው ተዘግቧል። ገበያው ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ አለው ።

ገበያው ንጉሴ

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች