የግብፅ ምርጫ እና የተከተለው ተቃውሞ | አፍሪቃ | DW | 29.05.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የግብፅ ምርጫ እና የተከተለው ተቃውሞ

በግብፅ የመጀመሪያው ዙር ፕሬዚደንታዊው ምርጫ ውጤት ትናንት ይፋ ሆኖዋል። በምርጫው ውጤት መሠረት፡ የሙስሊም ወንድማማችነት ፓርቲ ዕጩ መሀመድ ሙርሲ 24,3 ከመቶ ፡ የቀድሞ የግብፅ ፕሬዚደንት ሆስኒ ሙባራክ ዘመን ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩትን

የአህመድ ሻፊቅ ደግሞ 23,3 ከመቶ የመራጩን ድምፅ በማግኘት የፊታችን ሰኔ አጋማሽ ለሁለተኛ ዙር ምርጫ ይወዳደራሉ። ይህ ይፋ ከተነገረ በኋላ በአሌግዛንድርያ፡ በፖርት ሰይድ፡ በኢዝማይሊያ እና በስዌዝ ከተሞች የኃይል ርምጃ የታከለበት ተቃውሞ ተካሂዶዋል። በተለይ በመዲናይቱ ካይሮ የታህሪር አደባባይ የወጡ ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ተቃዋሚዎች የአህመድ ሻፊቅ የምርጫ ጽሕፈት ቤት ማዕከልን በእሳት አጋይተዋል። በዚሁ ጊዜም ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋ ግጭት ቢፈጠርም፡ ቀደም ሲል የጄዳው ወኪላችን ነቢዩ ሲራክ በስልክ እንደገለጸልን፡ በወቅቱ ሁኔታው የተረጋጋ ይመስላል።


ነቢዩ ሲራክ
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 29.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/1549L
 • ቀን 29.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/1549L