የግብፅ ሕገ-መንግሥት ማሻሻያና ተቃዉሞዉ | አፍሪቃ | DW | 20.03.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የግብፅ ሕገ-መንግሥት ማሻሻያና ተቃዉሞዉ

የግብፅ ሕዝብ ተሻሻለ የተባለዉን ሕገ-መንግሥት በመቃወም አደባባይ እንዲወጣ ቅስቀሳ ብጤ ጀምረዋል።የተቃዉሞዉ ሠልፍ የተቃደዉ ለመጪዉ ማክሰኞ ነዉ።መንግሥት የተቃዋሚዎቹን እቅድ ሲያዉቅ ለሰኞ ሕዝብ ዉሳኔ ጠራ።

የተቃዋሚ እንደራሴዎች ተቃዉሞ

የተቃዋሚ እንደራሴዎች ተቃዉሞ


የግብፅ ምክር ቤት ለጅም ጊዜ ሲሰራበት የነበረዉ የሐገሪቱ ሕገ-መንግሥት «እንዲሻሻል» ወሰነ።ተቃዋሚ የፖለቲካ ማሕበራት እና የመብት ተሟጋቾች ዉሳኔዉ የፕሬዝዳት ሆስኒ ሙባረክን እና የፖለቲካ ፓርቲያቸዉን ሥልጣን ይበልጥ የሚያጠናክር ነዉ በማለት አጥብቀዉ ተቃዉመዉታል። ማሻሻያዉ የሚፀናዉ በሕዝበ-ዉሳኔ ነዉ።ሕዝበ-ዉሳኔዉ በመጪዉ ሚያዚያ ይደረጋል ተብሎ ቢነገርም የሙባረክ መንግሥት የሚሰነዘርበትን የወቀሳ ጊዜ ለማሳጠር ሕዝበ ዉሳኔዉን በመጪዉ ሳምንት ለመጥራት አቅዷል።የርገን ሽትርይያክ ከካይሮ የዘገበዉን ነጋሽ መሐመድ አጠናክሮታል።

ባለፈዉ እሁድ የግብፅ ምክር ቤት የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ክርክር ላለዉ ጉባኤዉ እንደተሰየመ አንድ መቶ የሚሆኑ የተቃዋሚ የምክር ቤት እንደራሴዎች ጉባኤዉን ረግጠዉ ወጡ።በአብዛኛዉ ሙስሊም ወንድማማችነት የተባለዉ የአንጋፋዉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ከጉባኤዉ አዳራሽ ሲወጡም ሆኖ ካዳራሹ ደጃፍ ተቃዉሟቸዉን ሲያሰሙ የቴሌቪዥን ካሜራ ካጠገባቸዉ አልነበረም።የግብፅ ሕዝብ የከፊል እንደራሴዎቹን እርምጃ፣ ስሜትና ጩኸት ማየት አልቻለም።

ከሙስም ወድማማቾች መሪዎች አንዱ ኢሳም አል-አርያን ተቃዉሟቸዉን ለማሰማት የሐገራቸዉን ሳይሆን የቀጠርን ቴሌቪዥን ጣቢያ መጠበቅ ነበረባቸዉ።አል-ጀዚራን።

«NDP ዎች ዝምታ የመረጠዉን አብዛኛዉን ሕዝብ የነሱ ደጋፊ እንደሆነ ያቀርቡታል።ሕዝብ እንዳይሳተፍ፣ እንዳይደራጅ እራሳቸዉ አግደዉት ሲያበቁ፣ ሕዝቡ ከኛ ጋር ነዉ ይላሉ።

እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር ከ1980ዎቹ መጀመሪያ ወዲሕ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊደረግ የታቀደዉን ለዉጥ የፕሬዝዳት ሆስኒ ሙባረክ መንግሥት አሸባሪነትን ለመዋጋት ያለመ፣ ታላቅ የሕግ-መንግሥት ማሻሻያ ይለዋል።ሐቁ ግን ብዙዎች እንደሚሉት ተቃራኒዉ ነዉ።ለዘመናት ግብፅን በብረት ጡንቻ የገዙትን የሙባረክን እና ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የሚባለዉ ፓርቲያቸዉን አጋዛዝ ይበልጥ የሚያጠናክር፣ ተቃዋሚዎቻቸዉን የሚሸብብ ነዉ።

ፕሬዝዳት ሆስኒ ሙባረክ የሕዝቡን መብት ይበልጥ የሚያከብር የተሐድሶ ለዉጥ እንደሚያደርጉ ቃል መግባት ከጀመሩ ሁለተኛ አመታቸዉ።ለዉጡ ቃል የተገባዉ ሳይሆን ተቃራኒዉ ነዉ።የፍትሕ ተሟጋቾች፤ ጋዜጠኞች ወይም መገናኛ ዘዴዎች አንድም ታስረዋል አለያም እንዳሰሩ ታግደዋል።በቅርቡ እንኳን የሙባረክን አገዛዝ የተቸ የኢንተርኔት-አምደ መረብ አዘጋጅ ዘብጥያ ወርዷል።ከሁለት አመት በፊት በተደረገዉ ፕሬዝዳታዊ ምርጫ ከሙባረክ ቀጥሎ የሁለተኝነቱን ደረጃ ይዘዉ የነበሩት አል-ገሐድ-የተባለዉ ለዘብተኛ የፖለቲካ ማሕበር መስራች አይመን ኑር አምስት አመት እስራት ከተበየነባቸዉ አመት ሊደፍኑ ጥቂት ቀራቸዉ።

የገዢዉ ፓርቲ እንደራሴዎች አሁን በድምፅ ያፀደቁት የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ በተለይ አንቀፅ ሰላሳ-አራት በሐይማኖት ስም የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ማሕበራትን ያግዳል።ይሕ ወትሮም በሕግ የታገደዉን የሙስሊም ወድማቾች የፖለቲካ ማሕበረን ጨርሶ ለማጥፋት ያለመ ነዉ።ፓርቲዉ ሕገ-ወጥ ቢሆንም በግል ከተወዳደሩ አባላቱ ሰማንያ ስምንቱ የምክር ቤቱን እንደራሴነቱን ወንበር ይዘዋል።የገዢዉ ፓርቲ አባል ጊያድ ኦዳሕ ይሕንኑ ያረጋግጣሉ።

«እስላማዊ ወንድማማቾች በመሠረቱ ከረጅም ጊዜ በፊት በሕግ መታገዱን ማወቅ አለብሕ።እንደ ግለሰብ ግን አልታገዱም።ማንኛዉም ግለሰብ የራሱን አስተሳሰብ እና እምነት እንደፈለገዉ መግለፅ ይችላል።»

ይሕ በመንግሥትና በፖለቲካ ንቅናቄዎች መካካል የሚደረገዉ ትግል አካል ነዉ።አሁን የተወሰደዉ እርምጃ ከዚሕ ከፖለቲካዊዉ ሽኩቻ ባለፍ የሕግ ጉዳይ ነዉ ብዬ አላምንም።አይታየኝምም።

ማሻሻያ የተባለዉ የሕገ-መንግሥት ለዉጥ ግን የሙስሊም ወንድማማቾችን ብቻ ሳይሆን የግራ የፖለቲካ ማሕርሕ የሚከተሉትን፣ ለዘብተኞችንና ሌሎች ተቃዋሚዎችን በሙሉ የሚከትር ነዉ።አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አምንስቲ ኢንተርናሽናል የሕገ-መንግሥቱን ለዉጥ በግብፅ የሃያ-ስድስት አመት ታሪክ የዜጎችን መብት ለማገድ ከተወሰደዉ እርምጃ ሁሉ እጅግ ከባዱ በማለት ነቅፎታል።ሙባረክ የአገዛዝ ልጓማቸዉን ይበልጥ ያጠበቁት ከሳቸዉም በሕዋላ መንበራቸዉን ለልጃቸዉ ለገማል ለማስረከብ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ።

የካይሮ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳንይቲስት አሊ አል-ሰዋ እንዳሉትም ያሁኑ እርምጃ የእስካሁን ቅጣይ ነዉ።

«ይሕ በመንግሥትና በፖለቲካ ንቅናቄዎች መካካል የሚደረገዉ ትግል አካል ነዉ።አሁን የተወሰደዉ እርምጃ ከዚሕ ከፖለቲካዊዉ ሽኩቻ ባለፍ የሕግ ጉዳይ ነዉ ብዬ አላምንም።አይታየኝምም።»

የግብፅ ሕዝብ ተሻሻለ የተባለዉን ሕገ-መንግሥት በመቃወም አደባባይ እንዲወጣ ቅስቀሳ ብጤ ጀምረዋል።የተቃዉሞዉ ሠልፍ የተቃደዉ ለመጪዉ ማክሰኞ ነዉ።መንግሥት የተቃዋሚዎቹን እቅድ ሲያዉቅ ለሰኞ ሕዝብ ዉሳኔ ጠራ።